Wednesday, December 11, 2013

‘I have 29 children’: The ‘mothers’ to Ethiopia’s most vulnerable kids | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

‘I have 29 children’: The ‘mothers’ to Ethiopia’s most vulnerable kids | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

THE FUTURE IS IN OUR HANDS (Lij Imru Zelleke) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

THE FUTURE IS IN OUR HANDS (Lij Imru Zelleke) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

No More Green Terror in Saudi Arabia!! – by Tedla Asfaw | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

No More Green Terror in Saudi Arabia!! – by Tedla Asfaw | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider
የተከለከለ ~~--- ፍቅር - ሲፈቀር - ይገርም … እኮ! ምን ልበል ታዲያ ….


ከሥርጉተ ሥላሴ 11.12.2013


ፍቅር የትውልድ ዋዜማ ነው።
የመንፈስ ማዕቀብ ሲነሳ የነፃነት ፈል ችግኝ ይበቅላል በዚህ ልጀምረው ….
ፍቅር ምንድን ነው? ማድመጥ። ፍቅር ዜማ - ጹዑም! ፍቅር የመንፈስ ጥንግ ሽብሻባ። ፍቅር የስሜት ቃናዊ መዝሙር። ፍቅር የአኃቲነት ብርቅ ወረብ። ፍቅር የመስጠት ለጋስ ፏፏቴ። ፍቅር የታሪክ ማውጫ ፍትኃ - ነገሥት። ፍቅር የውስጥነት ፍውሰት - ድህነት! ፍቅር ጣዕም ንጥር - መረቅ! ፍቅር ብጡል* ክብረት። ፍቅር ምህረት። ፍቅር ይቅርታ። ፍቅር ረቂቅ። ፍቅር ቀጥታ። ፍቅር መሆን። ፍቅር ኃብታም ነው ዲታ። ፍቅር ምህረት ነው ዘንባባ! ፍቅር ወድ ነው ስጦታ። ፍቅር ሩህሩህ ነው ርግብ። ፍቅር ፈውስ የራህብ። ፍቅር ጻድቅ የመስቀል ወተት። ፍቅር የመስዋዕትነት ጤና አዳም። ፍቅርን ሲሰጡ ሊፈቀሩ የሚችሉ ፍጡራን ፍቅርን ሲከለከሉ ደግሞ ማመጻቸው አይቀሬ ነው!  ይፈነዳል።   ዋ!

እናት ከሁሉም በላይ ትውደዳለች። እናት የመጀመሪያዋ የህይወት ትምህርት ቤት ናት። እናት መቅድመ የቤተሰብ አሰተዳዳሪ፤ የተፈጥሮ ሙሁራ ሊቀ-ሊቃውንት የርህርህና መግቢያም።  እናት ደግሞ ሴት ናት። እኔ በዓለም ደረጃ የፍቅር ምልክት ወይንም ዓርማ ሊሆን የሚጋባው ልብ ሳይሆን እናት ነው መሆን ያለበት። ስለምን? እናት ልልጇ የምትሰጠው ፍቅር የማያብል ነውና። እውነተኛ የፍቅር ተፈጥሮ የሚገኘው ከስፖርት ማልያና ከእናት ብቻ ነው። እናት የሥነ ፍጥረት ሙሉዑ አጀንዳ ናት! እናት የመንፈስ ቋንቋ ናት!  ዬዓለም ተወዳጁ ሥም እማማ!

እስኪ ወፍ ካወጣን አብረን … ወደ ተለምኩት ብያለሁ፤ ቀልቤን ወደ ገዛው፤ ሩኼን ወደ ዳኘው። ጉዞ በጋራ መልካም ነው። ኑሮም በወል ጣዕሜ ነው። … ሴት እህት ስትሆን ትፈቀራለች። ሴት አክት ስትሆን ትጠጋላች። ሴት ሚስት ስትሆን እንደ ነፍስ ትታያለች። ሴት ጓደኛ ስትሆን ትታመናለች። ሴት እናት ስትሆን የጸጋ ስግደት ይሰገድላታል። ሴት ይሁን ይሁን … አሜን አሜን … ስትል ….. ሰጥ ለበጥ ብላ ስትገዛና ስትረገጥ …. ስትመች ትመረቃለች ….

እኔ እንደማስበው በእምነቴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አምስቱ አዕማደ ሚስጢራት ላይ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዑቅ ነገረ ሳይመር መቅረቱ በጣም ይጎረብጠኛል። እንደሚገባኝ ከሆነ ግን የተዋህዶ ልጆች ለቅድስት እናታችን ባለን ፍጹም ልዩ ፍቅርና ስስት ከጸጋ ስግደት ይልቅ የአምልኮ ስግደት ይገባታል ብለን እንዳንሟገት ብልሆቹ አቨው አስበውበት፤ ምንአልባትም መንፈስ ቅዱስም አቀብሏቸው ወይንም ሚስጢር ገልጦላቸው ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም ከመንፈሳዊ ዓለም ወጥተን ወደ ገኃዱ ዓለም ስንመጣ … በፖለቲካ አስተሳሰብ ሴት ላቅ ስትል ግን „ጉልበታምንት“ ይለጠፍላታል። በጠራ ቋንቋ „ጉልበታም“ ትባላለች። ገና ሳትታወቅ እፍታ መስመር ላይ እኮ ነው …. ልደቷን ሳታከብር የምትገፋው - ገምድልንት* የተከለከለ ፍቅር ይሏችኋል ይህ ነው። ቁስለት!

ሴት ረድ ስትሆን ትወደዳላች። ሴት ሎሌ ስትሆን ትደነቃለች። ሴት የቤት ውስጥ ሰራተኛ ስትሆን ስንዱ ትባላለች። ሴት ጠቅልል ጠቅለል አድርጋ ስታጎርስ የራህብ ደራሽ ትባላለች። ሴት ጓዳ ጉድ … ጉድ ስትል ዓይን አብሮ ይዞራል። መንፈስም አብሮ ይንከራተታል። ልብም ዳንኪራውን ያስነካዋል ስሜትም አብሮ ይከትማል። ፍቅሬ ወ/ሮዬ ትባላለች። ዓለም የፈጠረው ቄንጠኛ የዘነጠ ሥያሜ ሁሉ ይሰጣታል። ሴት እንግዳ ስታስተናግድ ትመሰገናለች። ሴት ልጅ ስትሰጥ በዓይኔ ላይ ፍሰሺ ትባላላች። ሴት ስልጣን ልትጋራ ብቅ ስትል ግን „ኃይለኛ“ ተብላ ትኮረኮማለች ወይንም ትባረራለች። ሌላ ድልዝ ይፈልግላታል። ሌላ የሰብዕናዋ ድክምት ቁፋሮ ይጀመራል።  የተከለከለ ፍቅር … ጎባጣ

ሴት ገንዘብ ያዥ ስትሆን ትመረጣለች። ሴት ገንዘብ ስትሰበስብ ታማኝነቷ ይሰበክላታል። ሴት እልፍኝ ስታሰናዳ ትሞካሻለች። ሴት ስነጥፍ ወይንም ስነጠፍ እንደ ብርቅ ትታያለች። ሴት ቅራኔ ውስጥ ገብታ ስተቀረቀር ይጨበጨብላታል። ሴት መድረክ ላይ ወጥታ አቅም ባላው ብቃት በፍፁም ታማኝነትና ግልጽነት እኩል ስትመጥን አቅሟን ለአደባባይ ስታበቃ ግን በግሳፄ ትባረራለች ….. ድገም ሳትል ከቢጫው ቀዩ ካርድ ቀድሞ ያለ ማስጠንቀቂያ ከጨዋታ ውጪ ትሆናለች። ነዳላ ገጠመኝ። የአንተ ያለህ ….

ሴት ስትለብስ ትፈቀራለች። ሴት ስተሸቀረቀር እንጉርጉሮው ላቅ - መጠቅ ይላላታል። ሴት የተፈጥሮን ፍቅር ስትመግብ ንቢት ተብላ ትሞገሳለች - ትመገባለች - ትጎረሳለችም። ሴት ሽክ ብላ ከጎን ስትጓዝና ግብዣ ላይ እኩል ስትቀመጥ አጃችን* ይሞላል ልጎዝጎዝልሽ ነው። ሴት ገብያ ወጥታ ቀጨር መጨሬውን ስትሸማምት አበጀሽ ትባላለች። ሴት ኮስሜቲክስ ስትገዛዛ ውዳሴ ይነጠፍላታል።  ሴት ወንበርን ልትጋራ ጥንካሬዋን ስታስመከር ግን ትገፈተራለች …. ቆመጥ ይዘጋጅላታል ….. የተከለከለ ፍቅርነቀዝ!

ሴት ቤት ስትውል፤ እንደ እመቤት ትታያለች፤ ጨዋ የተረጋጋ መንፈስ የረበባት እዬተባለ ይሰበክላታል። - ደስታ ነዋ ስታፎከፉክ። ሴት አንገቷን ደፍታ መከራን ስትቀበል ቅኔ ይዘረፍላታል። ሴት የልጆች አሳዳጊ ብቻ ስትሆን ትበረታታለች - ትሸለማለች። ሴት በማይታዩ ሩትን /ጥቃቅን/ ተግባራት ስትሰማራ ማን እንደ አንቺ ትባላለች። ሴት አንደበቷ ታስሮ የሳሎን ጌጥ ብቻ ስትሆን ማለፊያ ይባልላታል። ሴት ግን ኃላፊነትን እኩል ለመጋራት ጠበቅ ጠንከር ብላ ብቅ ስትል ጦር ይሰበቅባታል።  ያደገ ወይንም ያልተነካ ድንግል ወጥ ሃሳብ ወይንም ግኝት ወይንም ላቅ ያለነ የቀደመ ግንዛቤ  ስታፈልቅማ እሷንማ በሽታሽቶሽ* መውቃት።የተከለከለ ፍቅር …. ምግለት!

ሴት ስትጋግር … ስትሰራ …. ስታጥብ … ልብስ ስትተኩስ፤ ስታረግዝ …. ስታጠባ …. ከሚፈለገው ቦታ ላይ ተገኝታለችና ይዘፈንላታል። ከዚህ አለፍ ብላ የመብትና የእኩልነት ጥያቄ ስታነሳ ግን ትወረወራለች …. እውነት ለመናገር በዘመናችን ያሉ ሴቶች እንኳን ጥቃ ሊቆምላቸው፤ እንክብካቤ ሊያገኙ ቀርቶ ገፍተው የሚወጡት በጣም ጥቂቶች ለምነው ለመታገል እንኳን ፈቃድ አያገኙም በወንድ ትምክህተኞች …. ዛሬም ከዛሬ 100 ዓመት በፊት ካላው ኮረብታ ላይ እንዳሉ አሉ እነ ተባዕት …. ከእነ- የወንድ የበላይነት ተጫኝ ስሜታቸው ጋር ተጋብተው። ስለ ሴቶች ብዕራቸው በተቆርቋሪነት የሚቃኙት ከአንድ ለእናቱ  ሙሁር ከፕ/ አለማዬሁ ገ/ማርያም በስተቀር …. ፕሮፌሰሩ ከክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ጋር በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐሴትም አድምጠናል። ረስተውንም አያውቁም - ቅርባችን። ስለ ሴቶችን በሚያጠቃው የካንሰር በሽታ በተቆርቆሪነት የጻፉት ልብን የሚነካ ነበር። እውነት ልዩ አብነት ናቸው - ለእኔ። ድህነቴ እንጅ ለእሳቸው የምስጋና ቀን ባዘጋጅ ዕድለኛ በሆንኩ ነበር።

በፍጹም ሁኔታ የነፃነት ትግሉ ሆነ፤ ነገ የሚታሰበው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረቱና እርገቱ ከሴቶች ውጪ ሊታሰብም ሊሳካም እንደማይችል በጣም በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። የነፃነት ትግሉ የሴቶችን ሙሉዑ ተዋፆ በአጽህኖት፤ በተደሞና በአርምሞ ይጠይቃል። መደመጥ አለበት። አጥበቆ! አኔም የጥቃቱ ማዕደኛ በመሆኔ …. በልበ ሙለነት እጥፋለሁ … እንዲህና እንዲያ … ትርፉ ትራፊና ፍርፋሪ ካልሆነ ….

ይህቺ ለመላሾ እነ ተባዕት „ ቦታ አካፍለናል“ የሚሏት …. ልጥፍ ሽፋን ልግጫ ለማንም አይበጅም - ነገንም አያበጅ። የዶደመ …. መንገድ ነው። የነፃነት ትግሉ ሙሉዑነት ሊረጋገጥ የሚችለው የሴቶችን የመጠነ፤ ያስተዋለ፤ ያደመጠ፤ ያከበረ ተሳትፎ በቅንነት ተግባር ላይ ዛሬውኑ ሲያውል ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ካላት ያልተነካ ቅምጥ ዕምቅ ኃይል በላይ የሴቶች ሃብት እስከ ዛሬ ድረስ ሥራ ላይ አልዋለም። … ነገም ከፍቶት ይታዬኛል።

እርግጥ ማሳሳቻ አስፓልት አለ። „የሴቶች መምሪያ ከፍተናል … ጉዳያቸውን የሚከታተል መዋቅር ዘርግተናል“ … ይህ የሴቶችን ብቃት የሚያቀጭጭ አፋኝ የማስመሰያ ጅራፍ ነው። በአንድ ወቅት ፕ/ መራራ ጉዴናን አበክሬ እጠይቃቸው ስለ ነበር ንገሩልኝ የሴቶች መምሪያ በድርጅቴ መጀመሬን አሉ። የዛሬ 14 ዓመት መሆኑ ነው። አሁንም እሳቸው ከያዟት ቁልፍ ቦታ ግን ፈቀቅ አላሉም። ጨምድደው ጉብ ብለው ይለፉንም ዘግተው አሉ እንደ አገዱ። ይህ ትልቅ ግድፈት ነው። የእኔ ሙግት የነበረው በ2ኛው  የኢተፖድህ ጉባዔ ከዬትኛውም አባል ድርጅት አንድም የአንስት ውክል አካል ልትገኝ ደረጃዋ ባለመፍቀዱ ነበር - አበክሬ እናገር የነበረው።

ዘግይቶ የዛሬ ዓራት ዓመት ገደማ መደረክ ሲቋቋም አዬነው በመላጣ - ጎብጦ የሴቶችን እኩልነት በባዶ ቃላት ተለብጦ። ያው ቢገላበጡም ጃኬቱም ቢቀያዬር የተባዕት ክምር። የድርጀታቸውም አቅም … የወንዶች ብቻ - ቁልቁል። ይህ ለናሙና እንጂ በሽታው ሁሉንም ያካልላል። ከእከሌ ድርጀት እከሌ ይሻላል ብዬ ውዳሴ ባቀርብ የሴትነቴ ክብር ይዘቅጣል። ሴትነቴ ካለይግባኝ ዘቅዝቆ ይሰቅለኛል። ተፈጥሮም ፊቷን ታዞርብኛለች። አምላኬም ከልቡ ያዝንብኛል። ሃቁን ለከንቱ ውዳሴ ብሸብብ።*

በማናቸውም ዘርፈ እኔ ነኝ ባለ ወሳኝ ኃላፊነት ሁሉ ሴቶች ጉልበታም አቅም አላቸው። ለዛ የሚመጥን ቦታቸውን አትጋፉ ነው መሰረታዊ ትግሉ። አጽህኖታዊ መጠዬቁም። እድሉን ያገኙ ሴቶች ተዝርክርኮ ሳይሆን አምሮና ሰምሮ፤ በጥራትና በጥንቃቄ እንዲሁም በስልትና በብልኃት ሁለመናው ያምርበታል። ሴቶች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚተጉት …. በእናትነታቸው ፍጹም የማይታይ ሰማያዊ ጸጋ አስውበው ነው። ምቹ ሁኔታ  ካገኙ፤ በቂ እንክብካቤና ጥበቃ ለመክሊታቸው ከተደረገ …. ማን ችሏቸው። ያኮራሉ! ተወዳዳሪም የላቸውም። ሚስጢር ይመሰጠራል። ትርጉምም ይነበባል። ተፈጥሮም ይዘክራል። የሰብዕዊ መብት አከባበርም ጽኑ ባለሟል ሲገኝ በደስታ ይፍለቀለቃል። እኔ እላለሁ ሴቶች የተፈጥሮ ድንጋጌ ናቸውና።

አውሮፓ ያላችሁ ሁሉ እንደምትከታተሉት አውሮፓ በኢኮኖሚ ውጣ ውረድ ተሰቅዞ ሲባትልና ሲብተለተል የመፍትሄው ጭንቅላት የተገኘው አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ ማለቴ ነው ከጀርመን ነበር። የጀርመኗ መሪ ጠ/ሚ ወ/ሮ አንጅላ ሜርክል ቀጥ አድርገው በማያዝ ማገር ሆነው አውሮፓን ከውርዴት ዘመኑንም ከጥፋት ታድገውታል። ጠ/ሚር ሜርክል ፓን አውሮፓኒስት ናቸው። በተግባር የከበሩ የመጀመሪያዋ የጀርመን ተወዳጅ ሴት መሪ ናቸው። እርግጥ ከዚህ ጋር ያሉ ከፈረንሳይ ጋር የተሳሰረ ትብትብ ቢሮክራሲን  ዘልዬ …

ለናሙና …. የእንግሊዟ ታችር፤ ንግስት ኤልሳቢጥም፤ ተፍርተው በአጭሩ ተቀጩ እንጂ ልዕልት ዲያናም አሳይተዋል አስመስክረዋል … ያን ጉልበታም ተዝቆ የማያልቅ ብቃት …. ከብልህነት ጋር። ይህ በኒውዘላንድ፤ በአውስትራልያ፤ በፊላንድና በብራዚልም ተመሳጥሯል። ሲዊዘርላንድ በሰባት ሰዎች ትመራለች። አራቱ ሴቶች ናቸው። ያውም ቁልፍ ቁልፍ ቦታ የያዙ … በጀርመን ካለፈው ወራት ሀገራዊ ምርጫ በኋላ ያለውን ሽግሽግ አልተከታተልኩትም እንጂ ቀደም ባለው ጊዜ በርካታ ሴት ሚ/ራት ነበሩ …. የእውነት አባዛኞቹ ሴቶች በማለት ብቻ የሰከሩ አይደሉም። እናታዊ ሥነ -ምግባራቸው አይፈቅድላቸውምና! ይልቁንም በመሆን የበለጸጉ እንጂ …..

በዓለም በፈጠራ፤ በሳይንስና ምርምር፤ በሰብዕዊ ተግባር፤ እንዲሁም በሥነ - ጥበብ የበርካታ ምርጥ ዕንቁ ሴቶችን መዋዕለ ተጋድሎ፤ የያዘው የኖቤል ተሸላሚ ሴቶችን አስኪ ገድሉን ጎብኘት አድርጉት ….  እኔ በመንፈሴ እማማ ዊኒን፤ ሜርክልን እያጨሁ ነው። ብቁ ናቸዋ። በዬዓመቱ ከሲኤንኤን ጀግኖች ሴቶችም እኩላዊ ብቃታቸውን ለአደባባይ አብቅተዋል። እርግጥ እዬታፈኑ፤ ሳይታዩ እንዲጠፉ እዬታደመባቸው፤ እንዲከስሙ የተዘመተባቸው፤ እንዲሁም አስታዋሽና ጠበቃ ያጡት ሚሊዮኖች የነጻነት ሴት አርበኛ፤ የሥነ ተፈጥሮ ሁነኛ፤ የሥነ ጥበብ እማ ወራ … የፈጣራ ቀንዲል ዕልፍ ናቸው። የዓለም ብቁ ዜጎች ሴቶች መሆናቸው ምንም ለድርድር የሚቀርብ አይደለም። በአግባቡ ተከታታይና ባለቤት ቢኖረውማ …. በቁጥር ይበልጡም ነበር - በሁሉም ዘርፍ።    

ለሁላችንም የሚጠቅም ስለሆነ ደግሜ በመፃፌ እንደማላሰላችሁ በማሰብ በዘመነ ክሊንተን ያን የዓለም ስሜትን የሳበ የፕ/ ቢል ክሊንተን ተብዕታዊ ቅብጠት ብልኋ ባለቤታቸው እመቤት ሄነሪ ክሊንተን የሆነውን እንዳልሆነ አድርገው ትቢያ አልበሰውታል። በወቅቱ አንድ የፕሬስ ሰው እንዲህ ሲል ጠይቋቸው ነበር … „የሚባለውን አልሰማሽንም? … አላነበብሽውንም?“ ሲል ብልኋ እመቤት ግን መንፈሱ እንዲህ ነበር „ እናቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ያስተማረችኝ ሰው የሚለኝን ከሰማሁ የምሰራው የሰወችን እንጂ የእኔን እንዳልሆን ነግራኛለች፤ አስተምራኛለች። መርሄ ይህ ነው። እኔ የኔን ሥራ እሰራለሁ ሌሎች ደግሞ የራሳቸውን ይሰሩ“ ነበር ያሉት። ሰማዬ ሰማዬት የዘለቅ ዕጹብ መልስ ነበር። በዚህም ትዳራቸውን ከነዙፋኑ ሀገራቸውን ከነአልማዙ እስከብረዋል። አንስትን የወከለ ማለፊያ ብቃት!

ከዚህም በኋላ በዘመነ ፕ/ባራክ ኦባማ የውጭ ጉዳይ ሚር/ ሆነው እጅግ ውስብሰብና ፈታኝ በሆኑ መሰናክሎች ሁሉ በማለፍ የሴቶችን የመወስን አቅም በተግባር አሳብበውታል አሁንም የፕ/ ባራክ ኦባማ ባለቤት ቀዳማይ እመቤት ሚሻዬል ኦባማ ሁለገብ ንብ በመሆን ባለቤታቸውን ለሁለተኛ ጊዜ የሥልጣን ባለቤትነት አብቅተዋል … ለዚህም ደረጃ ያበቋቸው ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ሚሻዬል ናቸው። ነገም ለፕሪዚዳንትንት እራሳቸውን ችለው ሊወዳደሩ ይችላሉ። ተወዳጅም ናቸው - ወ/ሮ ሚሻዬል። ወንድሞቼ ሆይ! የነፃነት ትግሉ መሪ አባ ወራዎች ሆይ! ዓይን ካላችሁ ከዚህ ሀቅ ጋር የመንፈሳችሁ ብሌን ይታረቅ ዘንድ ብዕሬ በጽሞና ያሳስባችኋል … በአክብሮት - በትሁት መንፈስ።

በአፍሪካ ታሪክ ጉልበታሙ የፕ/ ማንዴላ ተገዳሎ የምዕተ ዓመቱ ታላቅ መዘክር ነው። ሚሊዮን ሰማዕት ሴቶች ታድመውበታል። በፆታዊ ችግር አፓርታይድ ያሴረውን መረብ ዝለሉትና ክብርት የነፃነት ብቁ አርበኛ እማማ ዊኒ ማንዴላ ባላቤቷ እስር ቤት በነበሩበት ጊዜ የነፃነት ትግሉን በግንባር በመምራት፤ ልጆቿን በማሳደግ፤ ለትዳር አጋራ አጥር ቅጥር በመሆን የጽናት ወተት ነበረች። ይህን ከባለቤቷ ጋር ትጻጻፍ ከነበረው የነፃነት ትግሉ ዋነኛ ትምህርት ቤት ዝክረ ደብዳቤዎች ማገናዘብ ይቻላል። ህያው ምስክር ነውና። ሁሉም ፍጡር እናቱን የሚወድበት ሚስጢር በሀገር ጉዳይ ላይ ቢውለው ምንያህል ፈውስ በነበረ - ለመለውዓለም። የ ዓለም ዝበርቅ አስፈሪ ውጣ ውረድ ፍቺ ያለው ከሴቶች ነበር … ባሊህ አጣ እንጂ …

በእኛዋ እናት ሀገርም … በቀደመው በዘመን ንግስት ዘውዲቱ የመቻልን ተፈጥሮ፤  ከእቴጌ ምንትዋብ የተግባር ሚስትነትና አርበኝነትን፤  ከከዕቴጌ ጣይቱ ብልህነት - ፖለቲካ መሪነትና አማካሪነት - ጠበብትነትና ጀግንነትን ጠብተን አድገናል። በዘመናችንም … ሳራ ግዛውና ሺብሬ በሰማዕትንተ፤  አያልነሽ - አለምዘውድ፤  ብርቱካን ሜዲቄሳ፤ ሰርካለም ፋሲል፤  ርዕዮት ዓለሙ፤ በላይነሽን ስንቶቹን የነፃነት አርበኞች እናት ሀገራችን አፍርታለች። መሬታች መሃን አይደለም። ተሳትፎውን በጉልበት ያነጠፈው* ያንጠፈጠፈውም የወንድ በላይነት ብቻ  ነው። አሁንም  በአንድነት ወ/ት ወይንሸት የምትሰጠውን ቃለ ምልልስ አኑትና አጣጥሙት …. ያው ታች ስለሆነች ቅጥቀጣው ያልፋታል ብዬም አስባለሁ … ቀና ካላች ግን ቅንጧን ነው … በለመደ እጅ … እህህህህህ!  

እኔ … በአጽህኖት እናገራለሁ። የፖለቲካ መሪዎቻችን የውስጥ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። በፍጥነት። በንግግራቸው ውስጥ እንኳን ብጣቂ እርስት አልተሰጠነም። እንኳንስ በፍላጎታቸው ልብ። በራዕያቸው አንጎልም የለንም። አብሰንት ነን።  ምንአልባት ትዝ የምንላቸው የራባቸው ጊዜ ይሆናል። ለነገሩ ነጭ ሀገር ፋስት ፉድም አለ … ዘመኑ ተለውጦ እራስም ይጋገራል … ሀገር ቤትም ተለምዷል አሉ … የጓዳ ነገር። እንዲሁም በዬአጋጣሚው የሚሾሟቸው አብዛኞቹ የበታች ገዢዎቻችንም ለውጡ ገፍቶ እንዲያነጥራቸው እንሻለን። አቅም በመበተንም አንቱ ናቸውና! ይደግም። የበታቾቻቸው አቅም በመበተን አንቱ ናቸውና!

የበላዮች የበታቾቸውን የሚከታተሉበት መስመር ቢኖር መልካም ነው። የጉሮሮ አጥንቶች እነሱ ናቸው። የፓለቲካ አመራር ልም ነው። ጣጣውን የጨረሰ ለስምሪት የበቃ ንጥር ቅቤም፤ ለስምሪትም ስንዱ። እኔ የማዬው ዘመንተኛው ፖለቲካ ግን ሽርክትና ግርድፍ ሆኖ ነው። አብሶ አጋርን በመገፍተር እረገድ ከንፍሮ የወጣ አንድም መሪ አልገጠመኝም። ቆሞ ስለ አርበኛ አንስት የሚመሰክር ዓይናችን አላዬም …. እንደናፈቃቸው ይቅር ዓይነት ነው ነገሩ …

እርግጥ ነው ሥር ላይ ያለው ተግባርን የሚያደምጡት፤ ከበታቾቻቸው ለዛውም ስታስቲክሱን በሩቁ ነው። ያው ወያኔ ባላው የተዛነፈ ዳታ ይወነጀላል። የኛም እኮ ያው ነው። ከታች ወደ ላይ የሚተላለፈው ቁጥር ተብዬ። የበቃ ፍጽምና ያለው ተሳትፎ …  ለማዬት ወረድ ይበሉ። ሰፊ መድረክ ይክፈቱ። የትችት አንባ ይወጁ። እንዲያድጉ እንዲመነደጉ ከፈለጉ። … በራስ አነሳሽነት የሚደረገው የፈጠራ ተሳትፎም እምብዛም ነው። ሁልጊዜ ከላይ የተንጠለጠለ መና ይጠበቃል። የማኒፌስቶውን ጭብጥ ይዞ ጭብጥን በጭብጥ አፋጭቶና አታግሎ የነጠረውን የፓርቲያቸውን አቋም አሸናፊ ለማድረግ ፈጠራ ከአቅም ጋር ይጠይቃል። ማረር!

ያው ቁንጮቹ የሚሉትን በተገኘው አጋጣሚ የጎረሱትን እዬፈቱ ሲደግሙና ሲሰልሱ ዓመት ይዞ እስከ ዓመት ከዛው ለዛው ሲዳክሩ ነው የሚታዩት። ተመስገን ነው ዛሬ እድሜ ለኢሳት በተለያዬ መድረኮች መሰናዶ ከሊቃኖች አዳዲስ ነገር ስንቅ ስለሚገኝ ተሽሎ ሊሆን ይችላል። ግን የራስ ጌታ ለመሆን ማንበብ መልካም ነገር ነው። የዬትም ሀገር ነፃነት ትግሎች ለድል እርከን ያደረሱት አጋራቸውን በበሰለ ህሊና ባሊህ ብለው ነው።  … እርግጥ ላይኞቹ ሴቶች ማለት ሲጀመሩ የታችኞች ቅጂውን እንደ ገደል ማሚቶ ያስተጋቡታልና እባካችሁ ላይኖቹ ጀመሩት …. ግን በተለበጠ መልኩ ሳይሆን ቁምነገር ባለው ዕውነት - ከልብም። ዝም ብሎ ከሆነ ልጥፍ ይሆንና የተላመጠ አገዳ ይሆናል ምኖታችን።
  
እኛ እንላላን። እኔና ትዳሬ ብዕሬ …. ተከታታይ የሆነ አቅም ያለው የመንፈስ ጥሪት ለመገንባት ይሞክሩ ፖለቲከኞቻችን ….፤ ሙሁሮቻችን። የሴቶችንም ነገረ ሚስጢር አክለው …. የሃይማኖት አባቶቻችን ሲያሰተምሩን „ነገረ መለኮትን“ ነጥለው ሳይሆን „ከነገረ ማርያም“ ተነስተውአስቀድመው እነሱ በቅድሰት ድንግል ፍቅር ቅጥል እያሉ ነው። የእናታቸው ፍቅር ግብግብ እያደረጋቸው ነው። እኛም እንደ እነሱ ሆነን እናታችን የማናሰነካው - ተከተል አባትህን ሆኖ ነው። የድንግል ነገር የሁለመናችን ገዢ የሆነውም በዚህው ቅኝት ተቀረጽን ስለሆን። ማለት ለተዋህዶ አማንያን። አሳምረው ጠረቡን። መንፈሳችን በቅዱስ መንፈስ ገሩት ነው። ያኑርልን ሊቀ - ሊቃውንቱን። የቅድስትን የመንፈስ ድንግልና ፍቅር በማያልቅ ወተት አጥብተው አሳድገውናልና። በሥጋዊ ፍቅርም ቢሆን ፍቅር ድብን አድርጎት እያለቀሰ ከልቡ የሚያዜም ከልብ ጠብ ይላል … በስተቀር ድው የለ ትም  ….

ይህ ትግል የሚባለው ጀግና … አርበኛና ሰማዕት …. ድሆኖው* ጉድሎበታል፤ ጎታው* ተራቁቶበታል ታላቅ ነገር ቅናዊ ዕይታ፤ ሥልጣንን የማጋራት ግልጽነት፤ ኃላፊነትን በቅመም የመመጠን ሥልጡን ዕይታ። ትርጉም ያለው ተግባራዊ እርምጃ ከኢትዮጵያዊነት መሪዎች በአጽህኖት ይጠበቃል።  እኩላዊ መስመር ሳይፈጠር አሯል። አይታይም። የመከነ ጉድ ነው …. በዬትኛውም ሁኔታ በቦታው የሌለ ነገር ቢኖር ሴቶችን  በአክብሮት እኩል ለማሳተፍ ያለው ፈቃደኝነት ልሙጥ መሆኑ ነው ድርቅ የተጫወተበት፤ ዝናብ ሲሄድበት የከረመ አለት የመሰለ ለዛ የለሽ ጉድ። በጣም በረቂቅ ሁኔታ በሴቶች ላይ የተጣለው ማዕቀብ ዘመንና ጊዜ ይፈታዋል የሚል ግምት የለኝም። የተሳሳረ ድንቡልቡል ነገር ነው። በሩ ተቀርቀሯል። ጭላንጭል መተንፈሿ ቧንቧው የታነቀ ነው ….  ለዛውም እኮ ቆርጠው የሚወጡት ጥቂት ሆነው እነሱን እንኳን በአግባቡ ለመያዝ ምንም …. ታውቃላችሁ?! ምንም ነው 00000 በቅናሴ ያለ … ተቋም ቢኖር …. የሴቶች የእኩልነት የተሳትፎ መድረክ ድርሻ ምክነት።

ህይወት ካለሴቶች ኮረኮንች --- አመዳም --- ቡላ ---- የፋደሰ ---- ቀዝቃዛ --- የነፈዘ ----- ነው የተፈቀፈቀ። …. የትግሉም ዕጣ ፈንታው ይህ እንዲሆን ተገምድሎበታል። ይፍታህ በሉት! ነይልኝ --- ነይልኝ --- „የህይወቴ ህይወት“ ለዚህ ብቻ  … ። ትውልድን በአዲስ የተሳትፎ ፖለቲካዊ ባህል ለመገንባት ዳገት። ታሪካዊ ድርሻን ለመወጣት ክትከታ። የምንፈለገው ለአጃቢነት ወይንም ጥላ ለመያዝ ወይንም ለዘበኝነት ብቻ። ደንበር ሰበር ለሆነ ለሚመጥን የሥልጣን ክፍፍል ወይንም ተደማጭነት ማነቆ - እገዳ - ክልከላ … ሰባራ ጉድ፤ …. ጨምዳዳ ….. ዕጣ። የተሸበሸበ … ራዕይ። ሽራፊ …. ህልም። ያመለ … ነገ። የሻገተ … ተስፋ። ያልተጠረገው መንገድ ረቂቅ ሚስጢር ይህን ይመስላል። መፍትሄው ለዛሬ አዲስ መኃንዲሶች፤ እራሳቸውን የዘለሉ ሙሴዎች ያስፈልጉታል … ይመስለኛል።

እናሳርገው። ….. የምቀኝነት በሽታ ያለባቸው ድውያን በዬአጋጣሚው ያፈኑት ነገር መተንፈሻ ከሌለው አጉል ቦታ ይፈስና ብዙ መስመሮችን ይበርዛል። „ልብ ያለው ሸብ“ ብለናል … ከብሂሉ ጋር እርገት ይሁን። እኔ ምን እንደሚናፍቀኝ ታውቃላችሁ ዓይነታ የወጣለት መሪ … ደፈር ብሎ ስለ ሴቶች …. ጥብቅና አጋፋሪ የሚሆን ሊጋባ። የነፃነት እልፍኝ አስከልካይ ሀቀኛ ዓራት ዓይናማ። ሴቶች ብዙ አላቸዋ። ያጡት ያላቸውን የሚያቀኑበት ገብያ ብቻ ነው ….. ግጥም ታውቃላችሁ … ቅኔዊ። እንደ ግጥም የልብን ድርስ የሚያደርጉ ምርጥ ፉጡራን ናቸው አብዛኞቹ ሴቶች። እርዳታቸው - ፈጣን፤ ምክራቸው የልብ አድርስ፤ ጽናታቸው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ፤ ፍቅራቸው የትውልድ ዋዜማ፤ ሥልታቸው ሥልጡን፤ ብልህነታቸው ተጨባጭን የዋጠ። ጉዟቸው ደፋር።

ሳልሄድበት የማልፈልገው ጥምዝ መንገድ ደግሞ ሌላው አጋር ለአጋር መገፋፋቱ ነው። ይህ ደግሞ ለአንስት የእኩልነት አንባ የከፋው ዕጣ ነውና ለአጋራችን እኛው አጋር በመሆን ጥጓ እንሁን። ብቃቷን ለመመስከር አንደበታችን እንፍታው፤ ለሴት እህታችን ብቃት ዋቢ እንሁንላት። ለሴት እህታችን ተጋድሎ ቀድመን እንገኝላት - ከጎኗ።  ለዘንካታ ትዕግስት ሞንሟና ምስጋና እንሆ!

ሴቶች የነፃነት ትግሉ ዓርማ ናቸው!
ሴቶች ለነጻነት ቅኔ ናቸው!
                                                  እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
  መፍቻ

  • አጃ የልብ መደረስ፤ ከጠበቁት በላይ መርካት።
  • ቅንጧን … ቅንድቧን …
  • ብጡል የተለዬ … የተመረጥ …
  • መገምደል … ፍትህን የጣሰ ፍርድ።
  • ያነጠፈው …. ያደረቀው … ምደረበዳ ያደረገው …. ድርቅ ያስመታው … ለዘር ያላበቃው ….
  • ሽታሽቶ  …. እያረፉ፤ በፈረቃ በድርብ …. ማድቀቅ …. ማጥቃት ….
  • መሸበብ … መሸፈን … መጋረድ … እንዳይታይ ማገድ …
  • ድሆኖ … ከጭቃ የሚሰራ መሰል ግጣም ያለው የእንጀራ መያዣ … ሌማት፤ ወይንም ጥራር እንደማለት
  • ጎታ … ከጭቃ የሚሳራ ትልቅ የ እህል መያዣ … እንደ በርሚል ….



የተከለከለ ~~— ፍቅር – ሲፈቀር – ይገርም … እኮ! ምን ልበል ታዲያ …. ከሥርጉተ ሥላሴ | Zehabesha Amharic

የተከለከለ ~~— ፍቅር – ሲፈቀር – ይገርም … እኮ! ምን ልበል ታዲያ …. ከሥርጉተ ሥላሴ | Zehabesha Amharic

Sunday, November 24, 2013

A poem dedicated to brothers and sisters in Saudi Arabiya. By Poet and human right activist Ato Ali Saeed | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

A poem dedicated to brothers and sisters in Saudi Arabiya. By Poet and human right activist Ato Ali Saeed | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ehiopian Embassy and Mouthpiece Teshaye Debalkew’s Photoshop Fails | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ehiopian Embassy and Mouthpiece Teshaye Debalkew’s Photoshop Fails | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

In repressive Ethiopia, new ‘Blue Party’ struggles to offer a choice | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

In repressive Ethiopia, new ‘Blue Party’ struggles to offer a choice | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

In repressive Ethiopia, new ‘Blue Party’ struggles to offer a choice | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

In repressive Ethiopia, new ‘Blue Party’ struggles to offer a choice | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ETHIOPIAN PROTEST AGAINST SAUDI ARABIA IN CHICAGO [Video] | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ETHIOPIAN PROTEST AGAINST SAUDI ARABIA IN CHICAGO [Video] | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ETHIOPIA’S DEMOCRATIC DILEMMA | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ETHIOPIA’S DEMOCRATIC DILEMMA | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

“Kafala” Persian Gulf Countries Enslavement System | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

“Kafala” Persian Gulf Countries Enslavement System | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

An open letter to Minister of Foreign Affairs (SMNE) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

An open letter to Minister of Foreign Affairs (SMNE) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Namibia: Ethiopia to Help Train Namibians

BY THERESIA TJIHENUNA, 22 NOVEMBER 2013
NAMIBIA and Ethiopia on Wednesday signed an agreement for health training programmes for Namibian health professionals, including doctors, nurses, technicians, pharmacists and paramedics.
The agreement was signed by the Ethiopian Health Minister Kesetebirhan Admasu and his Namibian counterpart Richard Kamwi in Windhoek.
As part of the MoU, the parties agreed that the Ethiopian government will provide Namibia with health professionals, experts and health-related tutors as well as to continue providing scholarships for an agreed number of Namibian students to Ethiopia.
Speaking at the signing ceremony, Kamwi said the two countries have similar health challenges of maternal deaths and communicable and non-communicable diseases, and it is only imperative that they learn from each other.
"We face the same challenges in the areas of communicable diseases such as HIV-AIDS, TB, diarrhoea, and childkiller diseases. This is in addition to the emerging non-communicable lifestyle diseases such as prostate, breast and cervical cancer, maternal mortality and malnutrition," he said. He also said the shortage of health workers of all categories in the countries was critical and that it was difficult to attract and retain health professionals in rural areas.
Kamwi said government has been gradually shifting resources to the disadvantaged regions, focusing on promotive, preventive and basic curative services provided by health centres, clinics, outreach services and community-based health care. "We currently have both public and private health sectors providing health services in the country, however, the collaboration between the two sectors needs to be strengthened," he said.
The Ethiopian government, he said, under its ministry of health, assisted Namibia with piloting the Health Extension Workers' Programme in the Kunene Region where 40 workers were trained.
The role of the extension workers is to promote disease prevention in communities, promote hygiene, sanitation and immunisation and perform maternal and child health assessments. Admasu said his country was winning the war against the health challenges it faced and that it was prepared to transfer the same health strategies to Namibia.
According to Kamwi, health extension programmes were rolled out in five regions with the assistance of the Ethiopian government, namely the Zambezi, Kavango, Ohangwena, Omusati and Kunene.
"A total of 565 Health Extension Workers are currently undergoing training in those regions this year," he said.
He said the Kunene pilot project was sponsored by Unicef and the EU, with the training of six months offered by the government of Ethiopia.

Retaliation to carnage on Ethiopians in Saudi Arabia. By Robele Ababya | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Retaliation to carnage on Ethiopians in Saudi Arabia. By Robele Ababya | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

To overcome the trouble that drives us to the Middle East let’s listen to an Oromo elder | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

To overcome the trouble that drives us to the Middle East let’s listen to an Oromo elder | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Wednesday, November 6, 2013

“ዶ/ር መረራ ጉዲና” እና “ኦቦ ሌንጮ ለታ” ከአፈንዲ ሙተቂ

የዶ/ር መረራን መፅሐፍ አነበብኩት፡፡ ታሪኩ በጣም ግሩም ነው፡፡ ዶ/ሩ በረጅሙ የህይወት ጉዞአቸው ያዩትን ነገር ነጥብ በነጥብ የሚያወጉበት ችሎታ አስደንቆኛል፡፡ እርግጥ መጽሐፉ በርካታ የፊደላት ግድፈት አሉበት፡፡ የአርታኢ እይታ የሚፈልጉ ቴክኒካዊ ጉድለቶችም ይታዩበታል፡፡

በዚህ ጽሑፍ በመጽሐፉ ላይ ሂሳዊ ግምገማ የማካሄድ ዓላማ የለኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ከመጽሐፉ እጠብቀው ከነበረውና ጸሓፊው (ዶ/ር መረራ) አለባብሰው ባለፉት አንድ ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ አንዳንድ ነገሮችን መወርወር እፈልጋለሁ፡፡me
***** ***** *****
ዶ/ር መረራ በገጽ-233 ላይ እንዲህ ይላሉ፡፡
“ከዲማ ኖጎ ቀጥሎ ያገኘሁት የኦነግ አመራር አባል ሌንጮ ለታን ነበር፡፡ የተገናኘነው በአጋጣሚ የአፍሪካ ጥናት ጉባኤ ማህበር የሚባለው በ1996 በቦስተን ከተማ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ነበር፡፡ ስብሰባው የተዘጋጀበት ትልቅ ሆቴል ስለነበር፡ የስብሰባው ቦታ ጠፍቶብኝ ኢትዮጵያዊ የሚመስል ፊት አይቼ ሰላም አልኩትና የስብሰባ ቦታውን ጠየቅኩት”፡፡ እርሱም ቦታውን ነገረኝና “ኢትዮጵያዊ ነህ ወይ?” አለኝ፡፡ “አዎን” አልኩትና ስሜን ነገርኩት፡፡ “ሌንጮ ለታ እባላለሁ፤ ለሁለንተናዊ ማብጠልጠልህ አመሰግናለሁ” አለኝ፡፡ ብዙም የሚያስጨንቀኝ ነገር ስላልነበረ “ያለፈው አልፏል፤ ጊዜ ካለህ ከስብሰባ በኋላ ትንሽ እናውራ” አልኩት፡፡ “የአየር መንገድ ቲኬቴ አያስችለኝም” አለኝ፡፡ ከኔ ጋር ብዙ ማውራት ፍላጎት እንደሌለው ስላሳየኝ ከዚያ በላይ አልገፋሁበትም፡፡”
አቶ ሌንጮ ለታ “ለሁለንተናዊ ማብጠልጠልህ አመሰግናለሁ” ያሉበት ምክንያት ምንድነው? ዶ/ር መረራ በመጽሐፋቸው አልገለጹትም፡፡ ከዚያ ይልቅ በጥንት ጊዜ ከሌንጮ ለታ ጋር የተዋወቁበትን አጋጣሚ ወደ መተረኩ ነው የተሸጋገሩት፡፡ ላለፉት ሀያ ዓመታት የኦሮሞ ድርጅቶችን የፖለቲካ አካሄድ በቅርበት ሲከታተል የነበረ ሰው ግን የሌንጮ አባባል የተሰነዘረበትን ምክንያት በደንብ ያውቃል፡፡ ዶ/ር መረራም በደንብ ያውቁታል፡፡ በርካታ ታዛቢዎችም ያውቁታል፡፡ ዶ/ር መረራ ምክንያቱን ያልገለጹት ለምንድነው? ያለፈ ታሪክ ስለሆነ ብንረሳው ይሻላል በማለት ነው? እርሳቸውና ድርጅታቸው በአሁኑ ጊዜ ከደረሱበት ደረጃ ጋር ስለማይመጣጠን ነው? ወይስ ሌላ ምክንያት አላቸው?
ዶ/ር መረራ መጻፋቸው ካልቀረ ሁሉንም ሊነግሩን በተገባ ነበር፡፡ እንዲያ ቢያደርጉ ደግሞ ለርሳቸውም ሆነ ለድርጅታቸው የንስሐ ያህል ይቆጠር ነበር፡፡ እንዲህ የምለው ከግል አቋም ተነስቼ አይደለም፤ እርሳቸው ያስቀየሟቸው በርካታ የህብረተሰብ ክፍል በመኖራቸው እንጂ፡፡ በርካታ ኦሮሞዎች ወደርሳቸውና ወደ ድርጅታቸው እንዳይቀርቡ ካደረጉት ነገሮችም አንዱ እርሳቸው ያኔ ሲፈጽሙት የነበረው ስህተት ነው፡፡ እስቲ ነገሩን በግልጽ ልጻፈው፡፡
***** ***** *****
በ1987 የመጨረሻ ወራት ነው፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና (ያኔ ረዳት ፕሮፌሰር ነበሩ) ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ህልውና ይበጃል ያሉትንና “በኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ አቅጣጫ-የባለብዙ ህብረተሰብ ዲሞክራሲን ማስፈን” የሚል ርዕስ የሰጡትን የፖለቲካ መጣጥፍ “ጦቢያ” በሚባለው መጽሔት ላይ አቀረቡ (ጦቢያ መጽሔት ቅጽ 10፤ ቅጽ 11 እና ቅጽ 12)፡፡ ያ በሶስት ክፍሎች ያሰናዱት ጽሑፍ የብዙዎችን ቀልብ ሳበ፡፡ በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ ሆነ፡፡ በብዙዎች ዘንድ በአድናቆት ተወደሰ፡፡ ከሌሎች ዘንድም ውግዘት ገጠመው፡፡ በጽሑፉ የተደሰቱት ዶ/ር መረራን “ጀግና፤ ሀቀኛ የኢትዮጵያ ልጅ፤ እውነተኛ ምሁር” አሏቸው፡፡ በጽሑፉ የተናደዱት ደግሞ “ጎበና፣ የኦሮሞ ህዝብን በድጋሚ ለመሸጥ ታጥቆ የተነሳ፤ ከሃዲ ወዘተ…” እያሉ አብጠለጠሏቸው፡፡ የጽሑፉ ደጋፊዎች መድረክ የነበረው እራሱ “ጦቢያ” መጽሔት ነበር፡፡ እርሱን በመጻረር የመልስ ጽሑፍ የሚከትቡት ደግሞ “ኡርጂ” እና “ሰይፈ ነበልባል” የተሰኙ ጋዜጦችን ይጠቀሙ ነበር (እርግጥ “ጦቢያ” መጽሔት በቅጽ 4 ቁጥር 3 እትሙ የመረራ ተቃራኒ የነበሩትን የዶ/ር መክብብ ገበየሁን ሰፊ መጣጥፍ አስነብቦን ነበር)፡፡
ዶ/ር መረራ በዚያ ጽሑፍ አጽንኦት የሰጡት ዋነኛ ነጥብ “የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በመገንጠል ሳይሆን በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ስር ይፈታል፤ ኦሮሞ ከብዛቱና ከስፋቱ ጋር የሚመጣን የፖለቲካ ስልጣን ቢጠይቅ ይሻላል፤ ለዚህም የአንድ ሰው አንድ ድምጽ መርህን መከተል አማራጭ የለውም” የሚል ነው፡፡ በመሰረቱ ይህ አመለካከት አዲስ አልነበረም፡፡ ከሜጫና ቱለማ ማህበር ምስረታ ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው፡፡ ከማህበሩ ታዋቂ አባላት መካከል የሚበዙት “ኦሮሞ በኢትዮጵያ ስር መሆን አለበት” ይሉ ነበር፤ የተቀሩት ደግሞ “ኦሮሞ ነጻ ወጥቶ ኦሮሚያ የምትባል ሀገር መመስረት አለበት” ባይ ነበሩ፡፡ በሂደት በማህበሩ ላይ የተወሰደው አፋኝና አሰቃቂ እርምጃ ግን አብዛኞቹ አባላት “ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ተለይቶ የራሱን ሀገር ካላቋቋመ በሰላምና በነጻነት መኖር አይችልም” የሚል አቋም እንዲይዙ አደረጋቸው፡፡
በውጪ ሀገር የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች በ1962 የትጥቅ ትግል ለመጀመር የሚያስችላቸውን ድርጅት በሚያቋቁሙበት ጊዜም የኦሮሚያ ነጻነት በሰፊው የተከራከሩበትና ወደፊት በጋራ እንፈታዋለን በማለት በይደር ያቆዩት ጉዳይ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን አንደኛው አመለካከት የበላይነትን አገኘ፡፡ በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች “የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል” የሚለውን መርህ የድርጅታቸው የትግል ዓላማ በማድረግ አጸደቁት፡፡ ከዚያ ወዲህም ይህ አመለካከት የብዙ ድርጅቶች ድምጽ ሆኖ ቆየ፡፡
ይሁንና እነዚያ ድርጅቶች የእስከ መገንጠል መርህን ስላጸደቁት ብቻ ሌላ አማራጭ ለኦሮሞ ህዝብ አያስፈልግም ማለት አይደለም፡፡ ማንም ሰው ለህዝቡ ይበጃል ያለውን የፖለቲካ አቅጣጫ በይፋ መስበክ ይቻላል፡፡ ሃሳቡን በየትኛውም መድረክ በነጻነት የመግለጽ መብት አለው፡፡ እርሱ ባቀረበው አማራጭ ሃሳብ ላይ ፍርድ የሚሰጠው ህዝብ ነው፡፡ ሃሳቡን ከግራና ከቀኝ መሞገት ቢቻልም ለህዝብ የማይጠቅም ነው ብሎ መደምደሚያ መስጠት አይቻልም፡፡ በግለሰብ ደረጃ ለማድረግ የሚቻለው የመሰለውን ተናግሮ የመጨረሻውን ብይን ለህዝብ ፍርድ መተው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ዶ/ር መረራን “ጎበና” እና “ከሀዲ” እያሉ አጥንት በሚሰብሩ ቃላት ሲወርፏቸው የነበሩት ጸሐፍት ትክክለኛ ነገር አልሰሩም፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲናም ልክ እንደነርሱ ስለኦሮሞ ህዝብ ችግር የመናገር ሙሉ መብት አለውና መናገር አትችልም የማለት መብት የላቸውም፡፡ በነዚያ ጸሐፍት ጎትጓችነት የተከሰተው ነገር ግን ከተጠበቀው ውጪ ሆኖ ነበር የተገኘው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
ዶ/ር መረራ በነዚያ የጋዜጣ አምደኞች ተረብና የብዕር ወቀጣ በጣም ነበር የተናደዱት፡፡ እናም የመሰላቸውን መልስ ሊሰጡአቸው ተነሱ፡፡ ምላሻው በመጽሔት ታትሞ ሲወጣ ግን በጣም አስደንጋጭ ሆነና አረፈው፡፡ ዶ/ር መረራ በርሳቸው ደረጃ ላይ ያለ ሰው ሊከተለው የሚገባውን ምሁራዊ ፈር በመልቀቅ ወደ ሰብቅና ተራ አሉባልታ ውስጥ ገቡ፡፡
በዚያን ወቅት ዶ/ር መረራ “የጽሑፍ ዘመቻ ከፍተውብኛል” ያሏቸው የኡርጂ እና የሰይፈነበልባል ዓምደኞች ጽሑፋቸውን በራሳቸው ስሜት ከማቀናበር ውጪ በየትኛውም ግለሰብ እና ድርጅት መወከላቸው አይታወቅም፡፡ ዶ/ር መረራ ግን ጸሐፊያኑን በአንድ ዘውግ በመጠቅለል የአንድ ቤተሰብ ምንደኞች ነበር ያስመሰሉት፡፡ ይህም የመልስ ጽሑፋቸውን በጀመሩበት ርዕስ ጭምር ጉልህ ሆኖ ይታይ ነበር (በወቅቱ የዶ/ር መረራ ጽሑፍ ከውስጠኛው የመጽሔቱ ክፍል ላይ “እነዚህ ልጆች ምን ይፈልጋሉ?” በማለት ይጀምራል፡፡ በመጽሔቱ የፊት ለፊት ሽፋን ላይ የሚታየው ርዕስ ግን “የሌንጮ ቡድን ምን ይፈልጋል?” የሚል ነው፤ ጽሑፉን ጦቢያ መጽሔት ቅጽ-4 ቁጥር አራት እና ቁጥር አምስት ላይ ያገኙታል)፡፡
ዶ/ር መረራ በዚያ ጽሑፍ መጀመሪያ ላይ “እስከዛሬ ድረስ ለኦሮሞ ህዝብ አንድነት ስንል የደበቅነውን ሐቅ ይፋ አወጣለሁ” የሚል ሐተታ አስቀምጠው ነበር፡፡ ሆኖም በጽሑፋቸው የተናገሩት አንዳች ሐቅ አልነበረም፡፡ ያ ጽሑፍ በርካታ የኦሮሞ ልጆች ለህዝባቸው የከፈሉትን መስዋዕነት ያኮሰሰ ነው፡፡ ከአንድ አካባቢ (ከወለጋ) የተገኙ የኦሮሞ ልጆችንም በጅምላ እንደ ወንጀለኛ የፈረጀ ነው፡፡ አልፎ ተርፎም የመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን አማኞችን “ከሚሲዮን ጸሎት ቤት የተፈለፈሉ የእንግዴ ልጆች” በማለት ተሳልቆባቸዋል፡፡
የዶ/ር መረራ ጽሑፍ በግለሰብ ደረጃ በሁለት ሰዎች ላይ ነበር ያተኮረው- ሟቹ ባሮ ቱምሳ እና አሁን በህይወት የሚገኘው ሌንጮ ለታ፡፡ በተለይ ግን የዶ/ር መረራ ጽሑፍ የስድብ መአት ያወረደው በባሮ ቱምሳ ላይ ነው፡፡ በኦሮሞ ህዝብ ትግል ውስጥ ለተከሰቱ ጥፋቶችና ድክመቶች ሁሉ ተጠያቂነቱን በዋናነት ለርሱ ይሰጣል፡፡ ባሮ ቱምሳን “ቁማርተኛ፤ በህዝብ ልጆች ደም ሲነግድ የኖረ፤ ለራሱ በመጋረጃ ተደብቆ እነ ጄኔራል ታደሰ ብሩን ለሞት አሳልፎ የሰጠ፤ በስልጣን ጥም የሰከረ የፖለቲካ እስስት” ወዘተ… ይለዋል፡፡ ጽሑፉ “ሌንጮ ለታና ባሮ ቱምሳ ሲታገሉ የኖሩት ለአንድ ቤተሰብ የፖለቲካ ሞኖፖሊ እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም አይደለም” ይልና ሌንጮን በባሮ ቱምሳ እግር ተተክቶ የቤተሰቡን ጥቅም ለማስከበር የሚራወጥ የከሰረ ነጋዴ አድርጎ ያቀርበዋል፡፡
የዶ/ር መረራ ጽሑፍ በጊዜው ራሳቸውን ለመከላከል ጠቅሞአቸው ይሆናል፤ ወይም “ጎበና” በመባላቸው የተነሳባቸውን ንዴት አብርዶላቸው ይሆናል፡፡ እውነታው ሲታይ ግን ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡ በዚያ ጽሑፍ የመጀመሪያው ተጎጂ የሆነው ህዝቡ ራሱ ነው፡፡ በርካቶች እንደሚያስታውሱት ዶ/ር መረራ ያንን ጽሑፍ በማቅረባቸው በህዝቡ መካከል ከፍተኛ ውዥንብር ተፈጥሮ ነበር፡፡ በተለይ በወቅቱ “እነዚህ ወለጋዎች አስጨፈጨፉን፤ ለነጻነት እንታገላለን ብለው ልጆቻችንን የእሳት እራት አደረጓቸው” እያሉ ያንሾካሹኩ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች የዶ/ር መረራን ጽሑፍ ሲያገኙ ማንሾካሸኩን ተውትና ወደ ግልጽ ዘለፋ ገቡ፡፡ “ይኸው! የወለጋዎችን ጉድ ተመልከቱ! እነዚህ ዜጎች የኦሮሞ ጠላቶች ናቸው” የሚሉ ድምጾችን መስማት ተጀመረ፡፡ የመረራ ጽሑፍ እንደ ማስረጃ እየተጠቀሰ በመጽሔትና በጋዜጣ ጭምር የወለጋ ኦሮሞዎችን ማብጠልጠልና ማጠልሸት የአንድ ወቅት ፋሽን ሆነ፡፡ ጠባብ ዘረኝነትን ለኦሮሞ ህዝብ ያስተማሩት የወለጋ ሰዎች ናቸው እስከ ማለት ተደረሰ፡፡ በዚያን ጊዜ የጀመረው ወለጋን ለይቶ የማጥቆር ዘመቻ እስከዚህ ዘመን ድረስ ዘለቀ (ዛሬም ብዙ ሰዎች ተመሳሳይ ስሜት ነው ያላቸው)፡፡
የዶ/ር መረራ ጽሑፍ ሌላኛው ጉዳት የተሳሳተ የታሪክ መረጃ ማስተላለፉ ነው፡፡ በተለይ የጽሑፉ ዋነኛ ማጠንጠኛ የሆነው ሰማእቱን አቶ ባሮ ቱምሳን ሰዎች እጅግ በተሳሳተ አኳኋን እንዲረዱት አድርጓል፡፡ ያኔ ይታተሙ የነበሩ አንዳንድ መጽሔቶችና አቶ አባዱላ ገመዳ የባሮ ቱምሳን አኩሪ የትግል ታሪክ አፈር ድሜ በመቀላቀል ለራሳቸው በሚያመቻቸው መንገድ የፈበረኩትን ታሪክ እንዲጽፉ መንስዔ ሆኖአቸዋል (ዶ/ር መረራ በአዲሱ መጽሐፋቸው “አባዱላ ገመዳ ከኔ መጽሐፍ ከአስር ጊዜ በላይ ጠቅሷል” የሚሉት የባሮ ቱምሳን ታሪክ በሚመለከተው ክፍል ነው)፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በጽሑፉ ለኦሮሞ ህዝብ ትግል አስተዋጽኦ ያደረጉ የሌሎች ሰዎች ታሪክም እየተዛነፈ ቀርቧል፡፡ በዚያ ጽሑፍ መነሻነት የጀመረው የሰዎችን ታሪክ የማዛነፍ አድራጎት ዛሬም ድረስ ቀጥሏል፡፡ ይህ በጣም ልብ የሚነካ ነገር ነው፡፡
በመሰረቱ የዶ/ር መረራ ጽሑፍ በስልጣን ጥመኛነትና በፖለቲካ እስስትነት የፈረጀው ባሮ ቱምሳና ቤተሰቡ እርሱ እንዳለው ሁሉንም ነገር በሞኖፖሊ የያዙ አልነበሩም፡፡ ከቤተሰቡ በቅድሚያ ወደ ፖለቲካው ዓለም የገባው ባሮ ቱምሳ ነው፡፡ የርሱ ወንድም የነበሩት ቄስ ጉዲና ቱምሳ በግልጽ ባይሆንም በስውር በትግሉ ውስጥ ተሳትፎ እንደነበራቸው ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም የቄስ ጉዲና ልጆች የሆኑት ታዋቂዋ ገጣሚ ሌንሳ ጉዲና እና ኩለኒ ጉዲና (የአቶ ዲማ ኖጎ ሚስት) በትግሉ ውስጥ ነበሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች በያኔው ትግል ውስጥ ሲገቡ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ከማበርከት ውጪ የኦሮሞ ህዝብ ትግልን በሞኖፖሊ የተቆጣጠሩበት ሁኔታ አልታየም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ሰዎች የባሮ ቱምሳ አማች አድርገው የሚቆጥሩት ሌንጮ ለታ ከባሮ ቱምሳ ጋር አንዳች ዝምድና አልነበረውም (የሌንጮ ሚስት “ማርታ ኩምሳ” ናት እንጂ በርካቶች እንደሚያወሩት “ማርታ ቱምሳ” አይደለችም)፡፡ ባሮ ቱምሳም ሆነ ቄስ ጉዲና ቱምሳ ለኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር ታግለዋል፡፡ በትግሉ ላይ እያሉ ተሰውተዋል፡፡ መላው የኦሮሞ ህዝብ ሁለቱንም ሰማዕታት በክብር ይዘክራቸዋል፡፡ ዶ/ር መረራ ግን እነኝህን ጀግኖች እንደ ዋልጌና ደም መጣጮች ነበር የቆጠሯቸው፡፡ ሆኖም የሚያውቃቸው በደንብ ያውቃቸዋል፡፡
***** ***** *****
ከላይ እንደገለጽኩት ሌንጮ ለታ በያኔው የዶ/ር መረራ ጽሑፍ የባሮ ቱምሳ ውርስ (legacy) አስቀጣይ ሆኖ ነበር የቀረበው፡፡ የስልጣን ፍርፋሪ ከማለም ውጪ ለዓላማ የማይታገል ወሸቤ ሆኖ ነው የተተረከው፡፡ ታዲያ በዚያ ወቅት ብዙዎችን ያስገረመው ነገር አቶ ሌንጮም ሆነ ድርጅቱ በመረራ ላይ ጣታቸውን ያልቀሰሩ መሆናቸው ነው፡፡ ዶ/ር መረራ ግን “ኡርጂ” እና “ሰይፈ ነበልባል” ጋዜጦችን ከጀርባ የሚያንቀሳቅሰው ሌንጮ ለታ ነው የሚሉ ይመስላሉ (እሳቸው በወቅቱ “የባህር ማዶ አለቆቻቸው” ነው ያሉት)፡፡ ለዚህም ነበር ጽሑፋቸው በቀጥታ በጋዜጠኞቹ ላይ ማነጣጠሩን ትቶ አፈሙዙን ወደ ሌንጮ ለታ ያዞረው፡፡ ለአባባላቸው ማስረጃ ያቅርቡ ቢባል ግን የላቸውም፡፡
የዶ/ር መረራ ጽሑፍ የሌንጮን የአመራር ድክመትና በትግል ዓለም የፈጸማቸውን ከባድ ስህተቶች እየነቀሰ አልተቸውም፡፡ አቶ ሌንጮ ለታ ድርጅቱን ሲመራበት የነበረውን አሰራርና የድርጅቱን አደረጃጀት ለመገምገም አልሞከረም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከሌንጮ ጋር እለያይበታለሁ ባለው የመገንጠል ጥያቄ ዙሪያ ታሪካዊና ማህበራዊ ጭብጦችን በመምዘዝ ድርጅቱ የሚከተለው መንገድ ለኦሮሞ ህዝብ የወደፊት እድል ጠንቅ የሚሆንበትን ምክንያት ለማስረዳት አልሞከረም፡፡ በቀጥታ የአንድ አካባቢ ተወላጆችን ወደ ማጥቃት ነው የገባው፡፡ እንዲህ ዓይነት ኢ-ምሁራዊ አካሄድን እንደ ፖለቲካ ስልት መጠቀም ስህተት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ነውር ነው፡፡
***** ***** *****
አቶ ሌንጮ ለታ ዶ/ር መረራን አሜሪካ ሲያገኘው “ለማብጠልጠልህ አመሰግንሀለሁ” ያለው ከላይ በቀረበው ምክንያት እንደሆነ ይገባኛል፡፡ የርሱ ከመረራ ጋር ለመነጋገር አለመፍቀድ አስደናቂ የማይሆነው ከጀርባው ይህንን የመሰለ ታሪክ ስላለ ነው፡፡ “ከሚሲዮን ጸሎት ቤት የተፈለፈሉ፤ የሚሲዮን ኬክ እየገመጡ ያደጉ” በሚሉ ጥሬ ቃላት ሰውን እየወረፉ እንነጋገር ቢሉ ማን ይሰማል?
አቶ ሌንጮ ለታ በቅርቡ አንድ አዲስ ድርጅት ፈጥሯል፡፡ የድርጅቱ ዓላማና መርህ በዶ/ር መረራ ጉዲና ከሚመራው ኦፌኮ ጋር በጣም ተቀራራቢ ነው፡፡ ሁለቱም “ኦሮሞ አይገነጠልም፤ የአንድ ሰው አንድ ድምጽ መርህ ይሻላል” ባይ ናቸው፡፡ እና እነዚህ ቡድኖች ተቀራርበው ይስሩ ቢባል በሁለቱ መሪዎች መካከል መተማመን ይፈጠራል? አይቻልም አይባልም መቼስ፡፡ ነገር ግን ሰዎቹን ማቀራረብ በጣም ያዳግታል፡፡ ያንን ጽሑፍ ያነበበ የሌንጮ ለታ ደጋፊ ዶ/ር መረራን አምኖ ወደ ፖለቲካው ለመጠጋት ያስቸግረዋል፡፡ የፖለቲካ መሪ በሚናገረውና በሚጽፈው ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡ ዛሬ በተሳሳተ ካምፕ ውስጥ ያለ አኩራፊ ሰው ነገ በባትሪ እንኳ ተፈልጎ የማይገኝ ወዳጅ ሊሆን ይችላል፡፡
***** ***** *****
ይህንን ሁሉ የጻፍኩት ለምንድነው ግን? የሌንጮ ለታ ወዳጅ ስለሆንኩ ነው? ወይስ መረራን ስለምጠላ? እኔ ከሁለቱም አይደለሁም፡፡ የመረራን መጽሐፍ ሳነብ የሌንጮ ለታ ነገር ተድበስብሶ ማለፉ ስለከነከነኝ ነው እውነታውን ወደ መጻፉ የገባሁት፡፡ በተለይ የያኔው የዶ/ር መረራ ጽሑፍ የተጫወተው አጥፊ ሚና ዛሬም ድረስ ወለል ብሎ የሚታየኝ በመሆኑ ዝም ብዬ ላልፈው አልፈቀድኩም፡፡ ዛሬም ድረስ በርካታ ሰዎች በወለጋ ኦሮሞዎች ላይ ያላቸው አሉታዊ አመለካከት አልተቀየረም፡፡ ጠባብነትና ጎጠኝነትን ከወለጋ ወገኖቻችን ጋር ማያያዝ አሁንም አልቀረም፡፡ የኦሮሞም ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝቦች ውድ ልጅ የሆነውን ባሮ ቱምሳን የጥፋት መልዕክተኛ አስመስሎ ማቅረብ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ዶ/ር መረራ ለዚያ አጥፊና አስደንጋጭ ጽሑፋቸው ይቅርታ አልጠየቁም፡፡ ስለዚህ ትውልድ እንዳይሳሳት የምናውቀውን ሁሉ ማሳወቅ አለብን፡፡
በቅርብ ጊዜ የሌንጮ ለታን መጽሐፍ ለማንበብ እቅድ አለኝ፡፡ ታዲያ እዚያም የተድበሰበሰ ነገር ከገጠመኝ ዝም ብዬ አላልፈውም፡፡ በተለይም በርሱ አመራር ዘመን ኦነግ የፈጸማቸው በርካታ ስህተቶችና ጥፋቶች እንደነበሩ በይፋ ስለሚታወቅ እነዚያን ጉድፎች አልሸፋፍንለትም፡፡ እነዚህ በተቃዋሚነት የተሰለፉ የፖለቲካ ሰዎቻችን ኢህአዴግንና በስሩ ያሉትን ድርጅቶች ብቻ መወረፍ እንጂ እነርሱን መንካት ያልተፈቀደልን ከመሰላቸው ተሳስተዋል፡፡ በተቃዋሚነት የተደራጀውም ሲያጠፋ የእጁን ሊያገኝ ይገባል፡፡ ቅንጅት፤ ኢህአፓ፤ መኢሶን፤ ኦነግ፣ ኦብነግ፤ ህብረት፣ ኢዴሐቅ፣ ኢፒዲአ፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ አረና እና ሌሎችንም መሔስና መገምገም እንችላለን፡፡ መሪዎቻቸውንም የመተቸት ሙሉ መብት አለን፡፡ በድሮ ዘመን “በገዳይ ስኳድ እንገድላችኋለን” የሚል ማስፈራሪያ ስለሚሰነዘር ማንም ሰው በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ያለውን ቅሬታ ውጦ ያስቀረው ነበር፡፡ አሁን ግን ፍራቻው የለም፡፡ ቢበዛ “የወያኔ ሰርጎ ገብ” ብንባባል ነው፡፡ ይህ ግን ሀገርና ህዝብን ከመጉዳት ውጪ የትም አያደርሰንም፡፡ ሁሉም ሀቁን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ በደርግ ቋንቋ “ሂስ የምትባለውን መራራ ኪኒን መዋጥ አለባችሁ” እንላቸዋለን፡፡
ሰላም!
አፈንዲ ሙተቂ

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ:

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ

Posted on November 3, 2013by syitda

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ: ተቀባይነት አላገኘም::#Ethiopia ሕወሓት ለወይዘሮ አዜብ ስልጣን በመስጠት በስልት ልታጠምዳቸው ነው::#TPLF
“ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው::” የሚሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት የሆኑት እና የሙስናዋ ወይዘሮ በመባል የሚታወቁት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለፓርቲያቸው ያቀረቡት የፖለቲካ በቃኝ ማመልከቻ ተቀባይነት ማጣቱ ሲገለጽ የሕወሓት ከፍተኛ ሰዎች ወይዘሮ አዜብን ለማጥመድ በሚያስችል ስልጣን ላይ ሊያስቀምቷቸው እንዳሰቡ ምንጮቹ ጠቁመዋል::የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው በወይዘሮ አዜባ ጋር በዋዛ አንላቀቅም በማለት ቂም በቀላቸውን ሊወጡባቸው ይችላሉ የሚል ግምቶች በሕወሓት አከባቢ እየተነገሩ ነው::
ለወይዘሮ አዜብ የታሰበው ስልጣን የትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በስልት ከፖለቲካ ለማፈግፈግ እና ለመልቀቅ ከአገር ለመውጣት እንደማይቻል ተነግሯቸዋል:: ወይዘሮ አዜብ በድጋሚ ማመልከቻ ማቅረባቸው እንደማይቀር የጠቆሙት ምንጮቹ ምንኛውም ስልጣን ቢሰጣቸው በአዲስ አበባ መስተዳደር ምክር ቤት ውስጥ አባል ሆነው የመቀጠል ፍላጎት እንዳሌላቸው በግልጽ ተናግረዋል::ባልቤቴ ከሞተ በኋላ በሕወሓት ተገፍቻለሁ የሚሉት ወይዘሮ አዜብ ምንም ነገር ሊመቻቸው እንዳልቻለ እና ስለ እሳቸው ውስጥ ለውስጥ የሚነዙ ፕሮፓጋንዳዎች እያበሳጯቸው እንደሆነ ተናግረዋል በተጨማሪም ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው ሲሉ አማረዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ.

Ethiopia arrests 2 journalists from independent paper (CPJ) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia arrests 2 journalists from independent paper (CPJ) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Thursday, September 19, 2013

Ethiopia urges Sudan and Egypt to implement panel’s report on Nile dam

By Tesfa-Alem Tekle
September 18, 2013 (ADDIS ABABA) - The Ethiopian government on Tuesday urged Sudan and Egypt to implement the final study report presented by the international panel of experts that was established to assess the impact of Ethiopia’s giant Nile dam project on downstream countries.
JPEG - 39.1 kb
Grand Ethiopian Renaissance Dam, when completed, will reduce the capacity of the Aswan High Dam, helping to save about six billion cubic metres of water. Image courtesy of Hajor.
Ethiopia cited the findings of the report issued last June as showing that the $4.7 billion Grand Renaissance dam will not have any significant effect on lower riparian countries of Egypt and Sudan.
“Ethiopia accepts the report and stresses the need for Egypt and Sudan to do so,” spokesperson for the ministry of foreign affairs ambassador Dina Mufti said.
Cairo says the construction of the massive hydro-electric dam project will diminish its water share, becoming its prime water security concern.
Addis Ababa however argues the dam project will regulate the flow of water avoiding flooding, reduce siltation and will allow provision of clean and cheap energy to Sudan and Egypt.
"Construction of the dam is underway taking into consideration the benefits of lower riparian countries” Mufti added.
The official dismissed some reports from Egyptian outlets and government officials who are labeling the project as a major threat to Egypt’s safety and security.
He said the reports are inappropriate and misleading.
An official told Sudan Tribune that nearly 30% of construction of the multi-billion power project is completed.
When the dam project - which will have power generation capacity of 6,000 MW - goes operational, the horn of Africa’s nation projects it will generate up to 2 million Euros per day from exporting hydro-electricity.
Although Ethiopia is a source to 85% of the Nile’s water resources, a colonial era treaty, however, has allowed Egypt to utilize the lion’s share of the water resources.
The treaty effectively granted the North African nation a veto power against any dam project along the Nile River in upper riparian countries.
Sudan however, has expressed support to Ethiopia’s dam project putting it at odds with Cairo.
(ST)

Dr. Negaso Gudada, Chairman of UDJ expressed his unreserved support for naming Andualem Aragie as the MAN OF THE YEAR | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Dr. Negaso Gudada, Chairman of UDJ expressed his unreserved support for naming Andualem Aragie as the MAN OF THE YEAR | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

2013 Sakharov Prize for Freedom of Thought – seven nominations | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

2013 Sakharov Prize for Freedom of Thought – seven nominations | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Million Voice for Freedom’s song | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Million Voice for Freedom’s song | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

The ethiopian renaissance or nuisance dam??? | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

The ethiopian renaissance or nuisance dam??? | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Challenge For Ginbot 7 leadership | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Challenge For Ginbot 7 leadership | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Wednesday, August 28, 2013

Dr. King’s Dream: An Ethiopian’s Perspective | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Dr. King’s Dream: An Ethiopian’s Perspective | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia: New Strategy Penned for Diaspora Housing Registration | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia: New Strategy Penned for Diaspora Housing Registration | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia: Growth likely to slow to 7% | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia: Growth likely to slow to 7% | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

The last remaining Jews from Ethiopia arrived in Israel. | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

The last remaining Jews from Ethiopia arrived in Israel. | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Struggling in Unison is Mandatory, Not an Option, Andinet Official | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Struggling in Unison is Mandatory, Not an Option, Andinet Official | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Oromo activist, Tesfahun Chemeda, dies in prison while serving life sentence | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Oromo activist, Tesfahun Chemeda, dies in prison while serving life sentence | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Dr asheber pimping for his own presidency (Video) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Dr asheber pimping for his own presidency (Video) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

U.S. Sen. Ted Cruz: ‘I am secretly a citizen of Ethiopia’ | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

U.S. Sen. Ted Cruz: ‘I am secretly a citizen of Ethiopia’ | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ESAT Radio: August 23, 2013 | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ESAT Radio: August 23, 2013 | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Polio Spreads to Ethiopia | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Polio Spreads to Ethiopia | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Telecoms in Ethiopia: Out of – The Economist | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Telecoms in Ethiopia: Out of – The Economist | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Tigrai Online’s hatemonger Mikael Abai unmasked – By Abebe Gellaw | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Tigrai Online’s hatemonger Mikael Abai unmasked – By Abebe Gellaw | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

A year after long time leader’s death, Ethiopia has seen little change | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

A year after long time leader’s death, Ethiopia has seen little change | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia: Recipe for Ethiopian Flatbread Remains a Treasured Secret | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia: Recipe for Ethiopian Flatbread Remains a Treasured Secret | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Corruption in the Ethiopian JUST US Sector – By Professor Alemayehu G. Mariam | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Corruption in the Ethiopian JUST US Sector – By Professor Alemayehu G. Mariam | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia: ESAT on the death of activist Tesfahun Chemeda in Kaliti jail | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia: ESAT on the death of activist Tesfahun Chemeda in Kaliti jail | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

I don’t know you, but I need to talk to you | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

I don’t know you, but I need to talk to you | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ESAT Eneweyay on Ethiopian opposition parties August 27, 2013 Ethiopia