Sunday, November 24, 2013

A poem dedicated to brothers and sisters in Saudi Arabiya. By Poet and human right activist Ato Ali Saeed | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

A poem dedicated to brothers and sisters in Saudi Arabiya. By Poet and human right activist Ato Ali Saeed | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ehiopian Embassy and Mouthpiece Teshaye Debalkew’s Photoshop Fails | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ehiopian Embassy and Mouthpiece Teshaye Debalkew’s Photoshop Fails | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

In repressive Ethiopia, new ‘Blue Party’ struggles to offer a choice | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

In repressive Ethiopia, new ‘Blue Party’ struggles to offer a choice | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

In repressive Ethiopia, new ‘Blue Party’ struggles to offer a choice | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

In repressive Ethiopia, new ‘Blue Party’ struggles to offer a choice | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ETHIOPIAN PROTEST AGAINST SAUDI ARABIA IN CHICAGO [Video] | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ETHIOPIAN PROTEST AGAINST SAUDI ARABIA IN CHICAGO [Video] | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ETHIOPIA’S DEMOCRATIC DILEMMA | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

ETHIOPIA’S DEMOCRATIC DILEMMA | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

“Kafala” Persian Gulf Countries Enslavement System | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

“Kafala” Persian Gulf Countries Enslavement System | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

An open letter to Minister of Foreign Affairs (SMNE) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

An open letter to Minister of Foreign Affairs (SMNE) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Namibia: Ethiopia to Help Train Namibians

BY THERESIA TJIHENUNA, 22 NOVEMBER 2013
NAMIBIA and Ethiopia on Wednesday signed an agreement for health training programmes for Namibian health professionals, including doctors, nurses, technicians, pharmacists and paramedics.
The agreement was signed by the Ethiopian Health Minister Kesetebirhan Admasu and his Namibian counterpart Richard Kamwi in Windhoek.
As part of the MoU, the parties agreed that the Ethiopian government will provide Namibia with health professionals, experts and health-related tutors as well as to continue providing scholarships for an agreed number of Namibian students to Ethiopia.
Speaking at the signing ceremony, Kamwi said the two countries have similar health challenges of maternal deaths and communicable and non-communicable diseases, and it is only imperative that they learn from each other.
"We face the same challenges in the areas of communicable diseases such as HIV-AIDS, TB, diarrhoea, and childkiller diseases. This is in addition to the emerging non-communicable lifestyle diseases such as prostate, breast and cervical cancer, maternal mortality and malnutrition," he said. He also said the shortage of health workers of all categories in the countries was critical and that it was difficult to attract and retain health professionals in rural areas.
Kamwi said government has been gradually shifting resources to the disadvantaged regions, focusing on promotive, preventive and basic curative services provided by health centres, clinics, outreach services and community-based health care. "We currently have both public and private health sectors providing health services in the country, however, the collaboration between the two sectors needs to be strengthened," he said.
The Ethiopian government, he said, under its ministry of health, assisted Namibia with piloting the Health Extension Workers' Programme in the Kunene Region where 40 workers were trained.
The role of the extension workers is to promote disease prevention in communities, promote hygiene, sanitation and immunisation and perform maternal and child health assessments. Admasu said his country was winning the war against the health challenges it faced and that it was prepared to transfer the same health strategies to Namibia.
According to Kamwi, health extension programmes were rolled out in five regions with the assistance of the Ethiopian government, namely the Zambezi, Kavango, Ohangwena, Omusati and Kunene.
"A total of 565 Health Extension Workers are currently undergoing training in those regions this year," he said.
He said the Kunene pilot project was sponsored by Unicef and the EU, with the training of six months offered by the government of Ethiopia.

Retaliation to carnage on Ethiopians in Saudi Arabia. By Robele Ababya | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Retaliation to carnage on Ethiopians in Saudi Arabia. By Robele Ababya | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

To overcome the trouble that drives us to the Middle East let’s listen to an Oromo elder | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

To overcome the trouble that drives us to the Middle East let’s listen to an Oromo elder | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Wednesday, November 6, 2013

“ዶ/ር መረራ ጉዲና” እና “ኦቦ ሌንጮ ለታ” ከአፈንዲ ሙተቂ

የዶ/ር መረራን መፅሐፍ አነበብኩት፡፡ ታሪኩ በጣም ግሩም ነው፡፡ ዶ/ሩ በረጅሙ የህይወት ጉዞአቸው ያዩትን ነገር ነጥብ በነጥብ የሚያወጉበት ችሎታ አስደንቆኛል፡፡ እርግጥ መጽሐፉ በርካታ የፊደላት ግድፈት አሉበት፡፡ የአርታኢ እይታ የሚፈልጉ ቴክኒካዊ ጉድለቶችም ይታዩበታል፡፡

በዚህ ጽሑፍ በመጽሐፉ ላይ ሂሳዊ ግምገማ የማካሄድ ዓላማ የለኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ከመጽሐፉ እጠብቀው ከነበረውና ጸሓፊው (ዶ/ር መረራ) አለባብሰው ባለፉት አንድ ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ አንዳንድ ነገሮችን መወርወር እፈልጋለሁ፡፡me
***** ***** *****
ዶ/ር መረራ በገጽ-233 ላይ እንዲህ ይላሉ፡፡
“ከዲማ ኖጎ ቀጥሎ ያገኘሁት የኦነግ አመራር አባል ሌንጮ ለታን ነበር፡፡ የተገናኘነው በአጋጣሚ የአፍሪካ ጥናት ጉባኤ ማህበር የሚባለው በ1996 በቦስተን ከተማ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ነበር፡፡ ስብሰባው የተዘጋጀበት ትልቅ ሆቴል ስለነበር፡ የስብሰባው ቦታ ጠፍቶብኝ ኢትዮጵያዊ የሚመስል ፊት አይቼ ሰላም አልኩትና የስብሰባ ቦታውን ጠየቅኩት”፡፡ እርሱም ቦታውን ነገረኝና “ኢትዮጵያዊ ነህ ወይ?” አለኝ፡፡ “አዎን” አልኩትና ስሜን ነገርኩት፡፡ “ሌንጮ ለታ እባላለሁ፤ ለሁለንተናዊ ማብጠልጠልህ አመሰግናለሁ” አለኝ፡፡ ብዙም የሚያስጨንቀኝ ነገር ስላልነበረ “ያለፈው አልፏል፤ ጊዜ ካለህ ከስብሰባ በኋላ ትንሽ እናውራ” አልኩት፡፡ “የአየር መንገድ ቲኬቴ አያስችለኝም” አለኝ፡፡ ከኔ ጋር ብዙ ማውራት ፍላጎት እንደሌለው ስላሳየኝ ከዚያ በላይ አልገፋሁበትም፡፡”
አቶ ሌንጮ ለታ “ለሁለንተናዊ ማብጠልጠልህ አመሰግናለሁ” ያሉበት ምክንያት ምንድነው? ዶ/ር መረራ በመጽሐፋቸው አልገለጹትም፡፡ ከዚያ ይልቅ በጥንት ጊዜ ከሌንጮ ለታ ጋር የተዋወቁበትን አጋጣሚ ወደ መተረኩ ነው የተሸጋገሩት፡፡ ላለፉት ሀያ ዓመታት የኦሮሞ ድርጅቶችን የፖለቲካ አካሄድ በቅርበት ሲከታተል የነበረ ሰው ግን የሌንጮ አባባል የተሰነዘረበትን ምክንያት በደንብ ያውቃል፡፡ ዶ/ር መረራም በደንብ ያውቁታል፡፡ በርካታ ታዛቢዎችም ያውቁታል፡፡ ዶ/ር መረራ ምክንያቱን ያልገለጹት ለምንድነው? ያለፈ ታሪክ ስለሆነ ብንረሳው ይሻላል በማለት ነው? እርሳቸውና ድርጅታቸው በአሁኑ ጊዜ ከደረሱበት ደረጃ ጋር ስለማይመጣጠን ነው? ወይስ ሌላ ምክንያት አላቸው?
ዶ/ር መረራ መጻፋቸው ካልቀረ ሁሉንም ሊነግሩን በተገባ ነበር፡፡ እንዲያ ቢያደርጉ ደግሞ ለርሳቸውም ሆነ ለድርጅታቸው የንስሐ ያህል ይቆጠር ነበር፡፡ እንዲህ የምለው ከግል አቋም ተነስቼ አይደለም፤ እርሳቸው ያስቀየሟቸው በርካታ የህብረተሰብ ክፍል በመኖራቸው እንጂ፡፡ በርካታ ኦሮሞዎች ወደርሳቸውና ወደ ድርጅታቸው እንዳይቀርቡ ካደረጉት ነገሮችም አንዱ እርሳቸው ያኔ ሲፈጽሙት የነበረው ስህተት ነው፡፡ እስቲ ነገሩን በግልጽ ልጻፈው፡፡
***** ***** *****
በ1987 የመጨረሻ ወራት ነው፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና (ያኔ ረዳት ፕሮፌሰር ነበሩ) ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ህልውና ይበጃል ያሉትንና “በኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ አቅጣጫ-የባለብዙ ህብረተሰብ ዲሞክራሲን ማስፈን” የሚል ርዕስ የሰጡትን የፖለቲካ መጣጥፍ “ጦቢያ” በሚባለው መጽሔት ላይ አቀረቡ (ጦቢያ መጽሔት ቅጽ 10፤ ቅጽ 11 እና ቅጽ 12)፡፡ ያ በሶስት ክፍሎች ያሰናዱት ጽሑፍ የብዙዎችን ቀልብ ሳበ፡፡ በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ ሆነ፡፡ በብዙዎች ዘንድ በአድናቆት ተወደሰ፡፡ ከሌሎች ዘንድም ውግዘት ገጠመው፡፡ በጽሑፉ የተደሰቱት ዶ/ር መረራን “ጀግና፤ ሀቀኛ የኢትዮጵያ ልጅ፤ እውነተኛ ምሁር” አሏቸው፡፡ በጽሑፉ የተናደዱት ደግሞ “ጎበና፣ የኦሮሞ ህዝብን በድጋሚ ለመሸጥ ታጥቆ የተነሳ፤ ከሃዲ ወዘተ…” እያሉ አብጠለጠሏቸው፡፡ የጽሑፉ ደጋፊዎች መድረክ የነበረው እራሱ “ጦቢያ” መጽሔት ነበር፡፡ እርሱን በመጻረር የመልስ ጽሑፍ የሚከትቡት ደግሞ “ኡርጂ” እና “ሰይፈ ነበልባል” የተሰኙ ጋዜጦችን ይጠቀሙ ነበር (እርግጥ “ጦቢያ” መጽሔት በቅጽ 4 ቁጥር 3 እትሙ የመረራ ተቃራኒ የነበሩትን የዶ/ር መክብብ ገበየሁን ሰፊ መጣጥፍ አስነብቦን ነበር)፡፡
ዶ/ር መረራ በዚያ ጽሑፍ አጽንኦት የሰጡት ዋነኛ ነጥብ “የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በመገንጠል ሳይሆን በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ስር ይፈታል፤ ኦሮሞ ከብዛቱና ከስፋቱ ጋር የሚመጣን የፖለቲካ ስልጣን ቢጠይቅ ይሻላል፤ ለዚህም የአንድ ሰው አንድ ድምጽ መርህን መከተል አማራጭ የለውም” የሚል ነው፡፡ በመሰረቱ ይህ አመለካከት አዲስ አልነበረም፡፡ ከሜጫና ቱለማ ማህበር ምስረታ ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው፡፡ ከማህበሩ ታዋቂ አባላት መካከል የሚበዙት “ኦሮሞ በኢትዮጵያ ስር መሆን አለበት” ይሉ ነበር፤ የተቀሩት ደግሞ “ኦሮሞ ነጻ ወጥቶ ኦሮሚያ የምትባል ሀገር መመስረት አለበት” ባይ ነበሩ፡፡ በሂደት በማህበሩ ላይ የተወሰደው አፋኝና አሰቃቂ እርምጃ ግን አብዛኞቹ አባላት “ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ተለይቶ የራሱን ሀገር ካላቋቋመ በሰላምና በነጻነት መኖር አይችልም” የሚል አቋም እንዲይዙ አደረጋቸው፡፡
በውጪ ሀገር የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች በ1962 የትጥቅ ትግል ለመጀመር የሚያስችላቸውን ድርጅት በሚያቋቁሙበት ጊዜም የኦሮሚያ ነጻነት በሰፊው የተከራከሩበትና ወደፊት በጋራ እንፈታዋለን በማለት በይደር ያቆዩት ጉዳይ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን አንደኛው አመለካከት የበላይነትን አገኘ፡፡ በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች “የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል” የሚለውን መርህ የድርጅታቸው የትግል ዓላማ በማድረግ አጸደቁት፡፡ ከዚያ ወዲህም ይህ አመለካከት የብዙ ድርጅቶች ድምጽ ሆኖ ቆየ፡፡
ይሁንና እነዚያ ድርጅቶች የእስከ መገንጠል መርህን ስላጸደቁት ብቻ ሌላ አማራጭ ለኦሮሞ ህዝብ አያስፈልግም ማለት አይደለም፡፡ ማንም ሰው ለህዝቡ ይበጃል ያለውን የፖለቲካ አቅጣጫ በይፋ መስበክ ይቻላል፡፡ ሃሳቡን በየትኛውም መድረክ በነጻነት የመግለጽ መብት አለው፡፡ እርሱ ባቀረበው አማራጭ ሃሳብ ላይ ፍርድ የሚሰጠው ህዝብ ነው፡፡ ሃሳቡን ከግራና ከቀኝ መሞገት ቢቻልም ለህዝብ የማይጠቅም ነው ብሎ መደምደሚያ መስጠት አይቻልም፡፡ በግለሰብ ደረጃ ለማድረግ የሚቻለው የመሰለውን ተናግሮ የመጨረሻውን ብይን ለህዝብ ፍርድ መተው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ዶ/ር መረራን “ጎበና” እና “ከሀዲ” እያሉ አጥንት በሚሰብሩ ቃላት ሲወርፏቸው የነበሩት ጸሐፍት ትክክለኛ ነገር አልሰሩም፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲናም ልክ እንደነርሱ ስለኦሮሞ ህዝብ ችግር የመናገር ሙሉ መብት አለውና መናገር አትችልም የማለት መብት የላቸውም፡፡ በነዚያ ጸሐፍት ጎትጓችነት የተከሰተው ነገር ግን ከተጠበቀው ውጪ ሆኖ ነበር የተገኘው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
ዶ/ር መረራ በነዚያ የጋዜጣ አምደኞች ተረብና የብዕር ወቀጣ በጣም ነበር የተናደዱት፡፡ እናም የመሰላቸውን መልስ ሊሰጡአቸው ተነሱ፡፡ ምላሻው በመጽሔት ታትሞ ሲወጣ ግን በጣም አስደንጋጭ ሆነና አረፈው፡፡ ዶ/ር መረራ በርሳቸው ደረጃ ላይ ያለ ሰው ሊከተለው የሚገባውን ምሁራዊ ፈር በመልቀቅ ወደ ሰብቅና ተራ አሉባልታ ውስጥ ገቡ፡፡
በዚያን ወቅት ዶ/ር መረራ “የጽሑፍ ዘመቻ ከፍተውብኛል” ያሏቸው የኡርጂ እና የሰይፈነበልባል ዓምደኞች ጽሑፋቸውን በራሳቸው ስሜት ከማቀናበር ውጪ በየትኛውም ግለሰብ እና ድርጅት መወከላቸው አይታወቅም፡፡ ዶ/ር መረራ ግን ጸሐፊያኑን በአንድ ዘውግ በመጠቅለል የአንድ ቤተሰብ ምንደኞች ነበር ያስመሰሉት፡፡ ይህም የመልስ ጽሑፋቸውን በጀመሩበት ርዕስ ጭምር ጉልህ ሆኖ ይታይ ነበር (በወቅቱ የዶ/ር መረራ ጽሑፍ ከውስጠኛው የመጽሔቱ ክፍል ላይ “እነዚህ ልጆች ምን ይፈልጋሉ?” በማለት ይጀምራል፡፡ በመጽሔቱ የፊት ለፊት ሽፋን ላይ የሚታየው ርዕስ ግን “የሌንጮ ቡድን ምን ይፈልጋል?” የሚል ነው፤ ጽሑፉን ጦቢያ መጽሔት ቅጽ-4 ቁጥር አራት እና ቁጥር አምስት ላይ ያገኙታል)፡፡
ዶ/ር መረራ በዚያ ጽሑፍ መጀመሪያ ላይ “እስከዛሬ ድረስ ለኦሮሞ ህዝብ አንድነት ስንል የደበቅነውን ሐቅ ይፋ አወጣለሁ” የሚል ሐተታ አስቀምጠው ነበር፡፡ ሆኖም በጽሑፋቸው የተናገሩት አንዳች ሐቅ አልነበረም፡፡ ያ ጽሑፍ በርካታ የኦሮሞ ልጆች ለህዝባቸው የከፈሉትን መስዋዕነት ያኮሰሰ ነው፡፡ ከአንድ አካባቢ (ከወለጋ) የተገኙ የኦሮሞ ልጆችንም በጅምላ እንደ ወንጀለኛ የፈረጀ ነው፡፡ አልፎ ተርፎም የመካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን አማኞችን “ከሚሲዮን ጸሎት ቤት የተፈለፈሉ የእንግዴ ልጆች” በማለት ተሳልቆባቸዋል፡፡
የዶ/ር መረራ ጽሑፍ በግለሰብ ደረጃ በሁለት ሰዎች ላይ ነበር ያተኮረው- ሟቹ ባሮ ቱምሳ እና አሁን በህይወት የሚገኘው ሌንጮ ለታ፡፡ በተለይ ግን የዶ/ር መረራ ጽሑፍ የስድብ መአት ያወረደው በባሮ ቱምሳ ላይ ነው፡፡ በኦሮሞ ህዝብ ትግል ውስጥ ለተከሰቱ ጥፋቶችና ድክመቶች ሁሉ ተጠያቂነቱን በዋናነት ለርሱ ይሰጣል፡፡ ባሮ ቱምሳን “ቁማርተኛ፤ በህዝብ ልጆች ደም ሲነግድ የኖረ፤ ለራሱ በመጋረጃ ተደብቆ እነ ጄኔራል ታደሰ ብሩን ለሞት አሳልፎ የሰጠ፤ በስልጣን ጥም የሰከረ የፖለቲካ እስስት” ወዘተ… ይለዋል፡፡ ጽሑፉ “ሌንጮ ለታና ባሮ ቱምሳ ሲታገሉ የኖሩት ለአንድ ቤተሰብ የፖለቲካ ሞኖፖሊ እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም አይደለም” ይልና ሌንጮን በባሮ ቱምሳ እግር ተተክቶ የቤተሰቡን ጥቅም ለማስከበር የሚራወጥ የከሰረ ነጋዴ አድርጎ ያቀርበዋል፡፡
የዶ/ር መረራ ጽሑፍ በጊዜው ራሳቸውን ለመከላከል ጠቅሞአቸው ይሆናል፤ ወይም “ጎበና” በመባላቸው የተነሳባቸውን ንዴት አብርዶላቸው ይሆናል፡፡ እውነታው ሲታይ ግን ጉዳቱ በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡ በዚያ ጽሑፍ የመጀመሪያው ተጎጂ የሆነው ህዝቡ ራሱ ነው፡፡ በርካቶች እንደሚያስታውሱት ዶ/ር መረራ ያንን ጽሑፍ በማቅረባቸው በህዝቡ መካከል ከፍተኛ ውዥንብር ተፈጥሮ ነበር፡፡ በተለይ በወቅቱ “እነዚህ ወለጋዎች አስጨፈጨፉን፤ ለነጻነት እንታገላለን ብለው ልጆቻችንን የእሳት እራት አደረጓቸው” እያሉ ያንሾካሹኩ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች የዶ/ር መረራን ጽሑፍ ሲያገኙ ማንሾካሸኩን ተውትና ወደ ግልጽ ዘለፋ ገቡ፡፡ “ይኸው! የወለጋዎችን ጉድ ተመልከቱ! እነዚህ ዜጎች የኦሮሞ ጠላቶች ናቸው” የሚሉ ድምጾችን መስማት ተጀመረ፡፡ የመረራ ጽሑፍ እንደ ማስረጃ እየተጠቀሰ በመጽሔትና በጋዜጣ ጭምር የወለጋ ኦሮሞዎችን ማብጠልጠልና ማጠልሸት የአንድ ወቅት ፋሽን ሆነ፡፡ ጠባብ ዘረኝነትን ለኦሮሞ ህዝብ ያስተማሩት የወለጋ ሰዎች ናቸው እስከ ማለት ተደረሰ፡፡ በዚያን ጊዜ የጀመረው ወለጋን ለይቶ የማጥቆር ዘመቻ እስከዚህ ዘመን ድረስ ዘለቀ (ዛሬም ብዙ ሰዎች ተመሳሳይ ስሜት ነው ያላቸው)፡፡
የዶ/ር መረራ ጽሑፍ ሌላኛው ጉዳት የተሳሳተ የታሪክ መረጃ ማስተላለፉ ነው፡፡ በተለይ የጽሑፉ ዋነኛ ማጠንጠኛ የሆነው ሰማእቱን አቶ ባሮ ቱምሳን ሰዎች እጅግ በተሳሳተ አኳኋን እንዲረዱት አድርጓል፡፡ ያኔ ይታተሙ የነበሩ አንዳንድ መጽሔቶችና አቶ አባዱላ ገመዳ የባሮ ቱምሳን አኩሪ የትግል ታሪክ አፈር ድሜ በመቀላቀል ለራሳቸው በሚያመቻቸው መንገድ የፈበረኩትን ታሪክ እንዲጽፉ መንስዔ ሆኖአቸዋል (ዶ/ር መረራ በአዲሱ መጽሐፋቸው “አባዱላ ገመዳ ከኔ መጽሐፍ ከአስር ጊዜ በላይ ጠቅሷል” የሚሉት የባሮ ቱምሳን ታሪክ በሚመለከተው ክፍል ነው)፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በጽሑፉ ለኦሮሞ ህዝብ ትግል አስተዋጽኦ ያደረጉ የሌሎች ሰዎች ታሪክም እየተዛነፈ ቀርቧል፡፡ በዚያ ጽሑፍ መነሻነት የጀመረው የሰዎችን ታሪክ የማዛነፍ አድራጎት ዛሬም ድረስ ቀጥሏል፡፡ ይህ በጣም ልብ የሚነካ ነገር ነው፡፡
በመሰረቱ የዶ/ር መረራ ጽሑፍ በስልጣን ጥመኛነትና በፖለቲካ እስስትነት የፈረጀው ባሮ ቱምሳና ቤተሰቡ እርሱ እንዳለው ሁሉንም ነገር በሞኖፖሊ የያዙ አልነበሩም፡፡ ከቤተሰቡ በቅድሚያ ወደ ፖለቲካው ዓለም የገባው ባሮ ቱምሳ ነው፡፡ የርሱ ወንድም የነበሩት ቄስ ጉዲና ቱምሳ በግልጽ ባይሆንም በስውር በትግሉ ውስጥ ተሳትፎ እንደነበራቸው ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም የቄስ ጉዲና ልጆች የሆኑት ታዋቂዋ ገጣሚ ሌንሳ ጉዲና እና ኩለኒ ጉዲና (የአቶ ዲማ ኖጎ ሚስት) በትግሉ ውስጥ ነበሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች በያኔው ትግል ውስጥ ሲገቡ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ከማበርከት ውጪ የኦሮሞ ህዝብ ትግልን በሞኖፖሊ የተቆጣጠሩበት ሁኔታ አልታየም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ሰዎች የባሮ ቱምሳ አማች አድርገው የሚቆጥሩት ሌንጮ ለታ ከባሮ ቱምሳ ጋር አንዳች ዝምድና አልነበረውም (የሌንጮ ሚስት “ማርታ ኩምሳ” ናት እንጂ በርካቶች እንደሚያወሩት “ማርታ ቱምሳ” አይደለችም)፡፡ ባሮ ቱምሳም ሆነ ቄስ ጉዲና ቱምሳ ለኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር ታግለዋል፡፡ በትግሉ ላይ እያሉ ተሰውተዋል፡፡ መላው የኦሮሞ ህዝብ ሁለቱንም ሰማዕታት በክብር ይዘክራቸዋል፡፡ ዶ/ር መረራ ግን እነኝህን ጀግኖች እንደ ዋልጌና ደም መጣጮች ነበር የቆጠሯቸው፡፡ ሆኖም የሚያውቃቸው በደንብ ያውቃቸዋል፡፡
***** ***** *****
ከላይ እንደገለጽኩት ሌንጮ ለታ በያኔው የዶ/ር መረራ ጽሑፍ የባሮ ቱምሳ ውርስ (legacy) አስቀጣይ ሆኖ ነበር የቀረበው፡፡ የስልጣን ፍርፋሪ ከማለም ውጪ ለዓላማ የማይታገል ወሸቤ ሆኖ ነው የተተረከው፡፡ ታዲያ በዚያ ወቅት ብዙዎችን ያስገረመው ነገር አቶ ሌንጮም ሆነ ድርጅቱ በመረራ ላይ ጣታቸውን ያልቀሰሩ መሆናቸው ነው፡፡ ዶ/ር መረራ ግን “ኡርጂ” እና “ሰይፈ ነበልባል” ጋዜጦችን ከጀርባ የሚያንቀሳቅሰው ሌንጮ ለታ ነው የሚሉ ይመስላሉ (እሳቸው በወቅቱ “የባህር ማዶ አለቆቻቸው” ነው ያሉት)፡፡ ለዚህም ነበር ጽሑፋቸው በቀጥታ በጋዜጠኞቹ ላይ ማነጣጠሩን ትቶ አፈሙዙን ወደ ሌንጮ ለታ ያዞረው፡፡ ለአባባላቸው ማስረጃ ያቅርቡ ቢባል ግን የላቸውም፡፡
የዶ/ር መረራ ጽሑፍ የሌንጮን የአመራር ድክመትና በትግል ዓለም የፈጸማቸውን ከባድ ስህተቶች እየነቀሰ አልተቸውም፡፡ አቶ ሌንጮ ለታ ድርጅቱን ሲመራበት የነበረውን አሰራርና የድርጅቱን አደረጃጀት ለመገምገም አልሞከረም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከሌንጮ ጋር እለያይበታለሁ ባለው የመገንጠል ጥያቄ ዙሪያ ታሪካዊና ማህበራዊ ጭብጦችን በመምዘዝ ድርጅቱ የሚከተለው መንገድ ለኦሮሞ ህዝብ የወደፊት እድል ጠንቅ የሚሆንበትን ምክንያት ለማስረዳት አልሞከረም፡፡ በቀጥታ የአንድ አካባቢ ተወላጆችን ወደ ማጥቃት ነው የገባው፡፡ እንዲህ ዓይነት ኢ-ምሁራዊ አካሄድን እንደ ፖለቲካ ስልት መጠቀም ስህተት ብቻ ሳይሆን ትልቅ ነውር ነው፡፡
***** ***** *****
አቶ ሌንጮ ለታ ዶ/ር መረራን አሜሪካ ሲያገኘው “ለማብጠልጠልህ አመሰግንሀለሁ” ያለው ከላይ በቀረበው ምክንያት እንደሆነ ይገባኛል፡፡ የርሱ ከመረራ ጋር ለመነጋገር አለመፍቀድ አስደናቂ የማይሆነው ከጀርባው ይህንን የመሰለ ታሪክ ስላለ ነው፡፡ “ከሚሲዮን ጸሎት ቤት የተፈለፈሉ፤ የሚሲዮን ኬክ እየገመጡ ያደጉ” በሚሉ ጥሬ ቃላት ሰውን እየወረፉ እንነጋገር ቢሉ ማን ይሰማል?
አቶ ሌንጮ ለታ በቅርቡ አንድ አዲስ ድርጅት ፈጥሯል፡፡ የድርጅቱ ዓላማና መርህ በዶ/ር መረራ ጉዲና ከሚመራው ኦፌኮ ጋር በጣም ተቀራራቢ ነው፡፡ ሁለቱም “ኦሮሞ አይገነጠልም፤ የአንድ ሰው አንድ ድምጽ መርህ ይሻላል” ባይ ናቸው፡፡ እና እነዚህ ቡድኖች ተቀራርበው ይስሩ ቢባል በሁለቱ መሪዎች መካከል መተማመን ይፈጠራል? አይቻልም አይባልም መቼስ፡፡ ነገር ግን ሰዎቹን ማቀራረብ በጣም ያዳግታል፡፡ ያንን ጽሑፍ ያነበበ የሌንጮ ለታ ደጋፊ ዶ/ር መረራን አምኖ ወደ ፖለቲካው ለመጠጋት ያስቸግረዋል፡፡ የፖለቲካ መሪ በሚናገረውና በሚጽፈው ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡ ዛሬ በተሳሳተ ካምፕ ውስጥ ያለ አኩራፊ ሰው ነገ በባትሪ እንኳ ተፈልጎ የማይገኝ ወዳጅ ሊሆን ይችላል፡፡
***** ***** *****
ይህንን ሁሉ የጻፍኩት ለምንድነው ግን? የሌንጮ ለታ ወዳጅ ስለሆንኩ ነው? ወይስ መረራን ስለምጠላ? እኔ ከሁለቱም አይደለሁም፡፡ የመረራን መጽሐፍ ሳነብ የሌንጮ ለታ ነገር ተድበስብሶ ማለፉ ስለከነከነኝ ነው እውነታውን ወደ መጻፉ የገባሁት፡፡ በተለይ የያኔው የዶ/ር መረራ ጽሑፍ የተጫወተው አጥፊ ሚና ዛሬም ድረስ ወለል ብሎ የሚታየኝ በመሆኑ ዝም ብዬ ላልፈው አልፈቀድኩም፡፡ ዛሬም ድረስ በርካታ ሰዎች በወለጋ ኦሮሞዎች ላይ ያላቸው አሉታዊ አመለካከት አልተቀየረም፡፡ ጠባብነትና ጎጠኝነትን ከወለጋ ወገኖቻችን ጋር ማያያዝ አሁንም አልቀረም፡፡ የኦሮሞም ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝቦች ውድ ልጅ የሆነውን ባሮ ቱምሳን የጥፋት መልዕክተኛ አስመስሎ ማቅረብ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ዶ/ር መረራ ለዚያ አጥፊና አስደንጋጭ ጽሑፋቸው ይቅርታ አልጠየቁም፡፡ ስለዚህ ትውልድ እንዳይሳሳት የምናውቀውን ሁሉ ማሳወቅ አለብን፡፡
በቅርብ ጊዜ የሌንጮ ለታን መጽሐፍ ለማንበብ እቅድ አለኝ፡፡ ታዲያ እዚያም የተድበሰበሰ ነገር ከገጠመኝ ዝም ብዬ አላልፈውም፡፡ በተለይም በርሱ አመራር ዘመን ኦነግ የፈጸማቸው በርካታ ስህተቶችና ጥፋቶች እንደነበሩ በይፋ ስለሚታወቅ እነዚያን ጉድፎች አልሸፋፍንለትም፡፡ እነዚህ በተቃዋሚነት የተሰለፉ የፖለቲካ ሰዎቻችን ኢህአዴግንና በስሩ ያሉትን ድርጅቶች ብቻ መወረፍ እንጂ እነርሱን መንካት ያልተፈቀደልን ከመሰላቸው ተሳስተዋል፡፡ በተቃዋሚነት የተደራጀውም ሲያጠፋ የእጁን ሊያገኝ ይገባል፡፡ ቅንጅት፤ ኢህአፓ፤ መኢሶን፤ ኦነግ፣ ኦብነግ፤ ህብረት፣ ኢዴሐቅ፣ ኢፒዲአ፣ ኢዴፓ፣ መድረክ፣ አረና እና ሌሎችንም መሔስና መገምገም እንችላለን፡፡ መሪዎቻቸውንም የመተቸት ሙሉ መብት አለን፡፡ በድሮ ዘመን “በገዳይ ስኳድ እንገድላችኋለን” የሚል ማስፈራሪያ ስለሚሰነዘር ማንም ሰው በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ያለውን ቅሬታ ውጦ ያስቀረው ነበር፡፡ አሁን ግን ፍራቻው የለም፡፡ ቢበዛ “የወያኔ ሰርጎ ገብ” ብንባባል ነው፡፡ ይህ ግን ሀገርና ህዝብን ከመጉዳት ውጪ የትም አያደርሰንም፡፡ ሁሉም ሀቁን ለመቀበል ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ በደርግ ቋንቋ “ሂስ የምትባለውን መራራ ኪኒን መዋጥ አለባችሁ” እንላቸዋለን፡፡
ሰላም!
አፈንዲ ሙተቂ

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ:

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ

Posted on November 3, 2013by syitda

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ: ተቀባይነት አላገኘም::#Ethiopia ሕወሓት ለወይዘሮ አዜብ ስልጣን በመስጠት በስልት ልታጠምዳቸው ነው::#TPLF
“ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው::” የሚሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት የሆኑት እና የሙስናዋ ወይዘሮ በመባል የሚታወቁት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለፓርቲያቸው ያቀረቡት የፖለቲካ በቃኝ ማመልከቻ ተቀባይነት ማጣቱ ሲገለጽ የሕወሓት ከፍተኛ ሰዎች ወይዘሮ አዜብን ለማጥመድ በሚያስችል ስልጣን ላይ ሊያስቀምቷቸው እንዳሰቡ ምንጮቹ ጠቁመዋል::የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው በወይዘሮ አዜባ ጋር በዋዛ አንላቀቅም በማለት ቂም በቀላቸውን ሊወጡባቸው ይችላሉ የሚል ግምቶች በሕወሓት አከባቢ እየተነገሩ ነው::
ለወይዘሮ አዜብ የታሰበው ስልጣን የትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በስልት ከፖለቲካ ለማፈግፈግ እና ለመልቀቅ ከአገር ለመውጣት እንደማይቻል ተነግሯቸዋል:: ወይዘሮ አዜብ በድጋሚ ማመልከቻ ማቅረባቸው እንደማይቀር የጠቆሙት ምንጮቹ ምንኛውም ስልጣን ቢሰጣቸው በአዲስ አበባ መስተዳደር ምክር ቤት ውስጥ አባል ሆነው የመቀጠል ፍላጎት እንዳሌላቸው በግልጽ ተናግረዋል::ባልቤቴ ከሞተ በኋላ በሕወሓት ተገፍቻለሁ የሚሉት ወይዘሮ አዜብ ምንም ነገር ሊመቻቸው እንዳልቻለ እና ስለ እሳቸው ውስጥ ለውስጥ የሚነዙ ፕሮፓጋንዳዎች እያበሳጯቸው እንደሆነ ተናግረዋል በተጨማሪም ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው ሲሉ አማረዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ.

Ethiopia arrests 2 journalists from independent paper (CPJ) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider

Ethiopia arrests 2 journalists from independent paper (CPJ) | Zehabesha – Latest Ethiopian News Provider